Popular Posts

Sunday, July 24, 2016

ዘመኑን ግዙ


እንግዲህ እንደ ጥበበኞች እንጂ ጥበብ እንደሌላቸው ሳይሆን እንዴት እንድትመላለሱ በጥንቃቄ ተጠበቁ፤ ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁ። ኤፌሶን ሰዎች 5፡15-16 
ብዙ ሰዎች የሚሳሳቱትና ከስኬት የሚወድቁት ቀኖቹ ለእነርሱ እንደሚሰራላቸው ባለማስተዋል በማሰብ ነው፡፡ ሰዎች ዘመኑ መልካም እንደሆነ ነገር ዘና ሲሉና በማስተዋል ካልነቁ እግዚአብሄር ወዳየላቸው የክብር ደረጃ መድረስ ያቅታቸዋል፡፡ 
ቀኖቹ ክፉዎች ናቸው፡፡ በጥንቃቄ ሳንኖር ቀኖቹ በራሳቸው ዝም ብለው ለእኛ ይሰራሉ ብለን ከጠበቅን አንሳሳታለን፡፡ ቀኖቹ በራሳቸው ለእኛ በጎነት አይሰሩም፡፡ መልካሙ የምስራች ግን እነዚህን ክፉ ቀኖች ለእኛ እንዲሰሩ ማድረግ መቻላችን ነው፡፡ እነዚህን ክፉ ቀኖች መግዛት የሚቻልበትና ለእኛ ስኬት እንዲሰሩ የሚደረግበት መላ አለ፡፡ 
ክፉ ቀኖች ለእኛ እንዲሰሩ ብሎም እግዚአብሄር ወዳየልን የህይወት አላማ መድረስ የምንችለው በጥበብ ጥንቃቄ ስንመላለስ ነው፡፡ 
የእግዚአብሄር ቃል በሚሰጠን ጥበብ ከተመላለስን እነዚህን ክፉ ቀኖች ገልብጠን ለእኛ በጎነት እንዲሰሩ ማድረግ እንችላለን፡፡ በሚበልጥ በእግዚአብሄር ጥበብ ከኖርን ክፋታቸው በእኛ ላይ እንዳይሰራ አድርገን ከሁኔታዎች ሁሉ በላይ መኖር እንችላለን፡፡ 
ከሕፃንነትህም ጀምረህ ክርስቶስ ኢየሱስን በማመን፥ መዳን የሚገኝበትን ጥበብ ሊሰጡህ የሚችሉትን ቅዱሳን መጻሕፍትን አውቀሃል። 2ኛ ጢሞቴዎስ 3፡15 
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ 
#ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መጋቢነት #ጥበብ #አቢይዋቁማ

No comments:

Post a Comment