Popular Posts

Thursday, September 14, 2023

የእግዚአብሔር #ጸጋ ተገልጦአል

ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጦአልና፤ ይህም ጸጋ፥ ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞት ክደን፥ የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እየጠበቅን፥ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል ወደ ቲቶ 2፡11-13

ሰዎች ካሉበት ከማንኛውም ጥፋት የሚያድናቸው የእግዚአብሔር ፀጋ ተገልጦዋል፡፡

የሰው ማንኛውም ችግር እና ጥፋት ምንጩ ሃጢያት ነው፡፡ ሃጢያት ሰውን ከእግዚአብሔር  ክብር አዋርዶ እንደሚጠፋ እንስሳት አስመስሎታል፡፡  

ሰው ግን ክቡር ሆኖ ሳለ አያውቅም፤ እንደሚጠፉ እንስሶች መሰለ። መዝሙረ ዳዊት 49፡12

ሃጢያት ሰውን ሁሉ ያዋርዳል ያሳንሳል ያጎሳቁላል፡፡ በአጠቃላይ ሃጢያት ሰውን ባሪያ ያደርጋል፡፡

ኢየሱስ መለሰ፥ እንዲህ ሲል፦ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ኃጢአት የሚያደርግ ሁሉ የኃጢአት ባርያ ነው።የዮሐንስ ወንጌል 8፡34

ሰውን ከሃጢያት እስራት ነፃ ማውጣት የሚችል ጉልበት ያለው የእግዚአብሔር ፀጋ ብቻ ነው፡፡

የእግዚአብሔር ፀጋ ጉልበት ሃጢያትን ያስክዳል፡፡ የእግዚአብሔር ፀጋ ሃያል የሆነውን አለማዊ ምኞትን ያስንቃል፡፡ የእግዚአብሔር ፀጋ እግዚአብሔርን የመምሰል ሃይልን ይሰጣል፡፡ ፀጋ በፅድቅ እንድንኖር አቅም ይሰጠናል፡፡

ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጦአልና፤ ይህም ጸጋ፥ ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞት ክደን፥ የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እየጠበቅን፥ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል ወደ ቲቶ 2፡11-13

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #ሃይል #ወንጌል #ፅድቅ #ሃጢያት #ቤተክርስቲያን #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #መስቀል #አቅም #ጉልበት  

No comments:

Post a Comment