Popular Posts

Friday, August 14, 2020

ፍቅር አይባክን

 

እኛ በጌታ በኢየሱስ አዳኝነት አምነን የዳንን እና የእግዚአብሄር ልጆች የሆንን ሁላችን የአባታችንን እግዚአብሄርን ፍቅር ተካፍለናል፡፡ የእግዚአብሄር ፍቅር በልባችን ፈሷል፡፡

በተሰጠንም በመንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን ስለ ፈሰሰ ተስፋ አያሳፍርም። ወደ ሮሜ ሰዎች 55

አሁን የሚያስፈልገን ፍቅር ስጠኝ ብለን ወደ እግዚአብሄር ከመፀለይ ይልቅ እግዚአብሄር በመንፈስ ቅዱስ በልባችን ያፈሰሰውን ፍቅር መጠቀም ጥበብ ነው፡፡

የእግዚአብሄርን ምህረት የተቀበልነው እንድናከማቸው ሳይሆን ሰዎች የእኛን ምህረትና ይቅርታ በሚፈልጉበት ጊዜ ለሌሎች ምህረትን እንድናከፋፍል ነው፡፡

ከዚያ ወዲያ ጌታው ጠርቶ፦ አንተ ክፉ ባሪያ፥ ስለ ለመንኸኝ ያን ዕዳ ሁሉ ተውሁልህ፤ እኔ እንደ ማርሁህ ባልንጀራህ የሆነውን ያን ባሪያ ልትምረው ለአንተስ አይገባህምን? አለው። የማቴዎስ ወንጌል 1832-33

በትልቁ ይቅር የተባልነው ይቅርታችንን በትንሹ ለሚፈልጉ ሰዎች ይቅርታን በቸርነት እና በደስታ እንድንሰጥ ነው፡፡

የሚመክርም ቢሆን በመምከሩ ይትጋ፤ የሚሰጥ በልግስና ይስጥ፤ የሚገዛ በትጋት ይግዛ፤ የሚምር በደስታ ይማር። ወደ ሮሜ ሰዎች 128

የእኛ ትልቁ በደላችን የተሸፈነው የሌሎችን በደል እንድንሸፍን ነው፡፡

ትጸልዩም ዘንድ በመጠን ኑሩ፤ ፍቅር የኃጢአትን ብዛት ይሸፍናልና ከሁሉ በፊት እርስ በርሳችሁ አጥብቃችሁ ተዋደዱ። 1 የጴጥሮስ መልእክት 48

ሰዎችን ካልወደድንበት በልባችን የፈሰሰው የእግዚአብሄር ፍቅር በከንቱ ይባክናል፡፡ በልባችን የእግዚአብሄር ፍቅር ፈስሶ እያለ ሰውን አለመውደድና ይቅር አለማለት ምግብን በመጋዘን አከማችቶ ሰው ሲራብ አይቶ ዝም እንደማለት ነው፡፡

ሰዎችን ላለመውደድ ይቅር ላለማለት እና ላለመማር ምንም ሰበብ የለንም፡፡ በልባችን የፈሰሰው የእግዚአብሄር ፍቅር የእኛን ምህረት ይቅርታና ፍቅር ለሚፈልጉ ሰዎች ሁሉ በቂ ነው፡፡ 

በልባችን የፈሰሰውን የእግዚአብሄርን ፍቅር እንድናከፋፍለው የተሰጠን ሃብት እንጂ የእኛ አይደለም፡፡ ካልተጠቀምነበት ብዙዎችን መባረክና ማንሳት የሚችለው ሃብት ይባክናል እንጂ አይጠራቀምም ለእኛም አይጠቅመንም፡፡

በተሰጠንም በመንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን ስለ ፈሰሰ ተስፋ አያሳፍርም። ወደ ሮሜ ሰዎች 55

Abiy Wakuma Dinsa አቢይ ዋቁማ ዲንሳ

ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.dinsa.37/notes

ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #ፍቅር #ስር #መሰረት #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #ቸርነት #ትግስት #ከቅዱሳንሁሉጋር #መታበይ #መመካት #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment