የምድር መሠረቶች የእግዚአብሔር ናቸውና!
ሰው በምድር ላይ እንዲበረክት አለመታበይ አለበት፡፡ ሰው በምድር ላይ ተቋቁሞ እንዲያልፍ የትቢትን ንግግር ማስወገድ አለበት፡፡ የትእቢተኛ ዋነኛ ተቃዋሚው እግዚአብሄር ነው፡፡ ስለዚህ ነው ሃና ስትፀልይ እንዲህ ያለችው፡፡
አትታበዩ፥ በኩራትም አትናገሩ፤ እግዚአብሔር አዋቂ ነውና፥ እግዚአብሔርም ሥራውን የሚመዝን ነውና፥ ከአፋችሁ የኵራት ነገር አይውጣ።
የእግዚአብሄርን በትእቢተኞች ላይ የሚያደርገውን ነገር የስራውን ዝርዝር ማወቅ ከፈለግን እንዲህ ተፅፎዋል፡፡ በተቃራው ትሁታንን እንዴት እንደሚያከብር በዚህ ክፍል እንመለከታለን፡፡
የኃያላንን ቀስት ሰብሮአል፥ ደካሞችንም በኃይል ታጥቀዋል። ጠግበው የነበሩ እንጀራ አጡ፤ ተርበው የነበሩ ከራብ ዐርፈዋል፤ መካኒቱ ሰባት ወልዳለችና፥ ብዙም የወለደችው ደክማለች።
በምድር ላይ ምንም ቋሚና የሚያስመካ ነገር የለም፡፡ በምድር ላይ ያለው ሁሉ ሃላፊና ጠፊ ነው፡፡ በትምክትህ እግዚአብሄር ከተቃወመህ ማንም አይደገፍህም፡፡ እግዚአብሄር በተቃወመህ ጊዜ ምንም ያህል ሃብትህ አያስጥልህም፡፡ ስልጣኑ ከእግዚአበሄር ተቃውሞ ያስመለጠው ሰው የለም፡፡
እግዚአብሔር ይገድላል ያድናልም፤ ወደ ሲኦል ያወርዳል፥ ያወጣል። እግዚአብሔር ድሀ ያደርጋል፥ ባለጠጋም ያደርጋል፤ ያዋርዳል፥ ደግሞም ከፍ ከፍ ያደርጋል።
ሃብትም ልጅም ስልጣንም ያልፋሉ፡፡ እግዚአብሄር ከተቃወመህ ሃብትህ አያጥልህም፡፡ በትቢትህ እግዚአብሄር ከተቃወመህ ልጅህና ትውልድህ አያድንህም፡፡
ከሕዝቡ መኳንንት ጋር ያስቀምጣቸው ዘንድ፥ የክብርንም ዙፋን ያወርሳቸው ዘንድ፥ ችግረኛውን ከመሬት ያስነሣል፥ ምስኪኑንም ከጉድፍ ያስነሣል፤
ከሃብት ከወገንም ከስልጣንም በላይ ፅኑ መሸሸጊያ አለመታበይ በኩራትም አለመናገር ነው፡፡ ለምን ቢባል ምድር ባለቤት አላት ፡፡ የምድርም ባለቤትዋም እግዚአብሄር ብቻ ነው፡፡ የምድር መሰረቶች የእግዚአብሄር ናቸውን፡፡
አትታበዩ፥ በኩራትም አትናገሩ፤ እግዚአብሔር አዋቂ ነውና፥ እግዚአብሔርም ሥራውን የሚመዝን ነውና፥ ከአፋችሁ የኵራት ነገር አይውጣ። የኃያላንን ቀስት ሰብሮአል፥ ደካሞችንም በኃይል ታጥቀዋል። ጠግበው የነበሩ እንጀራ አጡ፤ ተርበው የነበሩ ከራብ ዐርፈዋል፤ መካኒቱ ሰባት ወልዳለችና፥ ብዙም የወለደችው ደክማለች። እግዚአብሔር ይገድላል ያድናልም፤ ወደ ሲኦል ያወርዳል፥ ያወጣል። እግዚአብሔር ድሀ ያደርጋል፥ ባለጠጋም ያደርጋል፤ ያዋርዳል፥ ደግሞም ከፍ ከፍ ያደርጋል። ከሕዝቡ መኳንንት ጋር ያስቀምጣቸው ዘንድ፥ የክብርንም ዙፋን ያወርሳቸው ዘንድ፥ ችግረኛውን ከመሬት ያስነሣል፥ ምስኪኑንም ከጉድፍ ያስነሣል፤ የምድር መሠረቶች የእግዚአብሔር ናቸውና፥ በእነርሱ ላይም ዓለምን አደረገ። 1ኛ ሳሙኤል 2፡3-8
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakum...
No comments:
Post a Comment