“አስቀድማችሁ
ከፈሪሳውያን እርሾ ተጠበቁ፥ እርሱም ግብዝነት ነው።” የሉቃስ ወንጌል 12፡1
ፈሪሳዊነት
የአስተሳሰብ ዘይቤ ችግር ነው፡፡ ፈሪሳዊነት ትኩረት የሚሰጠውን ያለመስጠት ትኩረት የማይሰጠውን ከፍተኛ ትኩረት የመስጠት የዋጋ
አሰጣጥ መዛባት ችግር ነው፡፡ ፈሪሳዊነት ከመንፈሳዊነት ወደ ታይታ የተለወጠ የተሳሳተ የህይወት ዝንባሌ ነው፡፡
እነርሱም
ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን ትምህርት እንጂ ከእንጀራ እርሾ እንዲጠበቁ እንዳላላቸው ያን ጊዜ አስተዋሉ። የማቴዎስ ወንጌል 16፡12
የፈሪሳዊነት አስተሳሰብ ውድ የሆነውን የከበረውን
መንፈሳዊ ህይወት ርካሽ በሆነው በውጭ ታይታ ብቻ የመለወጥ አደገኛ አስተሳሰብ ነው፡፡ ካልተጠነቀቅን በፈሪሳዊያን ትምህርት በቀላሉ
ልንወሰድ እና የመንፈሳዊ ህይወት ዋጋ ሊጠፋብን ይችላል፡፡
እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ በውስጡ ቅሚያና ስስት ሞልቶ ሳለ የጽዋውንና የወጭቱን ውጭ ስለምታጠሩ፥ ወዮላችሁ። አንተ ዕውር ፈሪሳዊ፥ ውጭው ደግሞ ጥሩ እንዲሆን አስቀድመህ የጽዋውንና የወጭቱን ውስጡን አጥራ። እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ በውጭ አምረው የሚታዩ በውስጡ ግን የሙታን አጥንት ርኩሰትም ሁሉ የተሞሉ በኖራ የተለሰኑ መቃብሮችን ስለምትመስሉ፥ ወዮላችሁ። እንዲሁ እናንተ ደግሞ በውጭ ለሰው እንደ ጻድቃን ትታያላችሁ፥ በውስጣችሁ ግን ግብዝነትና ዓመፀኝነት ሞልቶባችኋል። የማቴዎስ ወንጌል 23፡25-28
የህይወት መውጫ የሆነውን ልብን ከመጠበቅ ይልቅ
የውጭውን የታይታ ልብስን በመጠበቅ የሚያምን አስተሳሰብ ያለው ማንኛውም ሰው ፈሪሳዊ ነው፡፡
አጥብቀህ ልብህን ጠብቅ፥ የሕይወት መውጫ ከእርሱ ነውና። መጽሐፈ ምሳሌ 4፡23
አቢይ
ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma
Dinsa
#ኢየሱስ #ጌታ #ፈሪሳውያን
#ግብዝነት #የአምልኮትመልክ
# #ጻፎች #ቤተክርስቲያን
#መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #ሰዱቃውያን
No comments:
Post a Comment