Popular Posts

Monday, July 31, 2023

አስቀድማችሁ ከፈሪሳውያን እርሾ ተጠበቁ! ክፍል 3

 

አስቀድማችሁ ከፈሪሳውያን እርሾ ተጠበቁ፥ እርሱም ግብዝነት ነው።የሉቃስ ወንጌል 121

የፈሪሳዊያን ትምህርት ተጠበቁ ሲባል አንድን የህብረተሰብ ክፍል ወይም አንድን ሃይማኖት የሚመለከት በፍፁም አይደለም፡፡

የፈሪሳዊነት አስተሳሰብ እኔ ስጋ ውስጥ አለ ፣ አንተ ስጋ ውስጥ አለ እንዲሁም አንቺ ስጋ ውስጥ አለ፡፡

ፈሪሳዊነት ካለእውቀት የሆነ የሃይማኖት ቅናት ነው፡፡ ካለእውቀት መቅናት እያንዳንዳችን ይብዛም ይነስም በህይወት ዘመናችን የሚያጋጥመን ድካም ነው፡፡

በእውቀት አይቅኑ እንጂ ለእግዚአብሔር እንዲቀኑ እመሰክርላቸዋለሁና። የእግዚአብሔርን ጽድቅ ሳያውቁ የራሳቸውንም ጽድቅ ሊያቆሙ ሲፈልጉ፥ ለእግዚአብሔር ጽድቅ አልተገዙም።ወደ ሮሜ ሰዎች 10፡2-3

ፈሪሳዊነት ለመንፈሳዊ ችግር መንፈሳዊ ያልሆነ መልስ ለመስጠት መሞከር ነው፡፡ ፈሪሳዊነት መንፈሳነትን በወግ እና በስርአት መተካት ነው፡፡ ፈሪሳዊነት ከዳንን በኋላ እግዚአብሔርን ማስደሰቻ መንገድን ትቶ በፈጠራ ችሎታ ሌላ ማስደሰቻ መንገድ ለመፍጠር መሞከር ነው፡፡  

ስለፈሪሳዊነት ሲነሳ እነርሱ እና እኛ ብለን ካሰብን ከትምህርቱ ተጠቃሚ ሳንሆን እንቀራለን፡፡ በገርነት እና በየዋህነት "እኔ እሆንን?" ማለት ህይወታችንን እንድንፈትሽ እና እንድንለውጥ ያስችለናል፡፡

እውነትንም ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል አላቸው። የዮሃንስ ወንጌል 8፡32

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

#ኢየሱስ #ጌታ #ፈሪሳዊ #ግብዝነት #የአምልኮትመልክ # #ፃፎች #ቤተክርስቲያን #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #ሰዱቃዊያን


No comments:

Post a Comment