Popular Posts

Monday, August 28, 2023

ወንጌልን የሚሰብኩ ከወንጌል ቀለብ እንዲቀበሉ ጌታ ደንግጎአል ክፍል 7

 

እንዲሁ ደግሞ ወንጌልን የሚሰብኩ ከወንጌል ቀለብ እንዲቀበሉ ጌታ ደንግጎአል። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 9፡14

ወንጌልን የሚሰብኩ ሁሉ በመፅሃፍ ቅዱስ ላይ በግልፅ በተጻፈው በእግዚአብሔር አሰራር ማመን አለባቸው፡፡ የእግዚአብሔር ህዝብ አገልጋዮቹን በደንብ መንከባከብ እንዳለበት ሁሉ ወንጌልን የሚሰብኩ ስለኑሮዋቸው የገቢ ምንጭ የእግዚአብሔር ቃል የሚለውን አምነው መቀበል ይኖርባቸዋል፡፡

ወንጌልን የሚሰብኩ በወንጌል ከመኖር ይልቅ ከተፃፈው ውጭ ለራሳቸው ሌላን መንገድ ማዘጋጀት የለባቸውም፡፡

አንዳንድ የወንጌሉ ሰባኪዎች ስለመሰረታዊ ፍላጎታቸው መሟላት በእግዚአብሔር ላይ ከመታመን ይልቅ የራሳቸውን ዘዴ ይቀይሳሉ፡፡ አንዳንዶቹ እግዚአብሔር ሳይናገራቸው የቤተክርስቲያንን የገቢ ማስገኛ ንግድ ያቋቁማሉ፡፡

አንዳንዶቹ ደግሞ ቤተክርስቲያን በህዝቡ መስጠት ላይ እንዳትደገፍ የራስዋ የገቢ ማስገኛ ሌሎች መንገዶች ያደራጃሉ፡፡

የወንጌሉ ሰባኪዎች በዋነኝነት በመፅሃፍ ቅዱስ ስለእነርሱ በተፃፈው በእግዚአብሔር የአቅርቦት አሰራር ላይ ብቻ መደገፍ ይኖርባቸዋል፡፡ እግዚአብሔርም ያልተናገራቸውን ተጨማሪ ገቢ ማስገኛ በማቋቋም ለቅዱሳን ነፍስ ከመትጋት መደናቀፍ የለባቸውም፡፡ ይልቁንም በእምነት በእግዚአብሔር አሰራር ላይ በመታመን ለቅዱሳን አገልግሎት መትጋት ይጠበቅባቸዋል፡፡

ነገር ግን ቃሉን የሚማር ከሚያስተምረው ጋር መልካምን ነገር ሁሉ ይከፋፈል። ወደ ገላትያ ሰዎች 6፡6

ከእግዚአብሔር አሰራር ውጭ የሆነ ማንኛውም የገቢ ማስገኛ ዘዴ የእግዚአብሔርን ምሪት የሚጠይቅ ነው፡፡ እንዲያውም እግዚአብሔር በግልፅ ካልተናገረ በስተቀር የቤተክርስትያንን ውጤታማነት ሊቀንስ የሚችል አደገኛ አካሄድ ነው፡፡

ለራስህ ታላቅን ነገር ትፈልጋለህን? በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ፥ እነሆ፥ ክፉ ነገርን አመጣለሁና አትፈልገው፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ነገር ግን በሄድህበት ስፍራ ሁሉ ነፍስህን እንደ ምርኮ አድርጌ እሰጥሃለሁ። ትንቢተ ኤርምያስ 45፡5

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

#ኢየሱስ #ጌታ #ገንዘብ #ቀለብ #ወንጌል #ኑሮ #ስጡ #ቤተክርስቲያን #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #ገቢ


No comments:

Post a Comment