Popular Posts

Sunday, August 6, 2023

የተመሳሳይ ፆታ ችግር የአዲሱ ኪዳን መፍትሄ

ግብረ ሰዶምነት የእግዚአብሔርን ተፈጥሮ አላግባብ መጠቀም ነው፡፡ ግብረሰዶማዊነት ሃጢያት ነው፡፡ ግብረሰዶማዊነት ክቡር ፍጥረትን ላልተፈጠረበት አላማ በማዋል ማጎሳቆል ነው፡፡

ስለ ግብረሰዶማዊነት ችግር እና መፍትሄ መፅሃፍ ቅዱስ በብሉይ ኪዳንም ይሁን በሃዲስ ኪዳንም ይናገራል፡፡

እግዚአብሔር እንደ ህገ መንግስት ለእስራኤላዊያን በሰጣቸው በብሉይ ኪዳን ግብረሰዶማዊነት ያስገድል ነበር፡፡

አሁን የምንኖረው በአዲሱ ኪዳን ነው፡፡ በአዲሱ ኪዳን የእግዚአብሔር ለግብረሰዶማዊነት ያለው አቋም ባይለወጥም መፍትሄው ግን ተለውጦዋል፡፡

አሁን ግን በአዲስ ኪዳን ግብረሰዶማዊነት አያስገድልም፡፡ በአዲሱ ኪዳን ግብረሰዶማዊን እናስተምረዋለን እንሰብከዋለን እንጂ አንገድለውም፡፡

ወንጌልን መስበክ እና እግዚአብሔር በመጀመሪያ ወንድ እና ሴትን በእግዚአብሔር አምሳል እንደፈጠረ ከአፈጣጠሩ ማስተማር ይጠበቅብናል፡፡

የአዳም የትውልዱ መጽሐፍ ይህ ነው። እግዚአብሔር አዳምን በፈጠረ ቀን በእግዚአብሔር ምሳሌ አደረገው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው፥ ባረካቸውም። ስማቸውንም በፈጠረበት ቀን አዳም ብሎ ጠራቸው። ኦሪት ዘፍጥረት 5፡1-2

የሴት እና የወንድ ግንኙነት ብቻ የእግዚአብሔርን ሙሉ መልክ እንደሚያንፀባርቅ የእግዚአብሄን የጥንቱን አላማ ማስተማር ይጠይቃል፡፡

የእውነትን ቃል በቅንነት የሚናገር የማያሳፍርም ሠራተኛ ሆነህ፥ የተፈተነውን ራስህን ለእግዚአብሔር ልታቀርብ ትጋ። 2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2፡15

ሰው በሬን አርዶ በብልት በብልቱ እንደሚለያየው ሁሉ መፅሃፍ ቅዱስን በብሉይ ኪዳን እና በአዲስ ኪዳን ለያይተን መከፋፈል አለብን፡፡

በመፅሃፍ ቅዱስም ውስጥ ቢሆን የተጻፈ ነገር ስናይ ለብሉይ ኪዳን ህዝብ ነው ወይስ ለአዲስ ኪዳን ህዝብ ነው የተፃፈው ብለን መለየት አለብን፡፡

እንደው መፅሃፍ ቅዱስ ውስጥ ስላየነው ብቻ የብሉይ ኪዳንን ትእዛዝ በአዲስ ኪዳን ለመፈፀም ስንሞክር እንሳሳታለን፡፡

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

#ኢየሱስ #ጌታ #ጋብቻ #ፍቅር #ተቃራኒፆታ #ወንድ #ሴት #ወንድእናሴት #ተመሳሳይፆታ #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #ትዳር  #ግብረሰዶም #ግብረሰዶማዊነት

 

No comments:

Post a Comment