የነቢይ ኢዩ ጩፋ የተቃራኒ ፆታ ችግር መፍትሄ
መፅሃፍ ቅዱሳዊ አይደለም
ነቢይ ኢዩ ጩፋ በአገራችን ላይ እየታየ ስላው
የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ተቃውሞ ያደረገው አጭር የቪድዮ መልእክት ተመልክቼዋለሁ፡፡
የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ተፈጥሮአዊም ሆነ መፅሃፍ
ቅዱሳዊ ግንኙነት ባለመሆኑ ሁላችንም በፅኑ ልንቃወመው ይገባል፡፡
ይህን ፅሁፍ ለመፃፍ ያነሳሳኝ የነቢት ኢዩ ጩፋ
ሁለተኛው መፍትሄ ሃሳብ ነው፡፡
በምክሩ ወጣቶች በየአካቢያቸው የተመሳይ ፆታ
ግንኙነት የሚፈፅሙትን እየፈለጉ ልብስ አስወልቀው አስፓልት ላይ አስቀምጠው እንዲገርፉ የመፍትሄ ሃሳብ ይሰጣል፡፡
እንደ እግዚአብሄር ሰው መፅሃፍ ቅዱሳዊ መሰረቱን
መናገር እና ማስተማር ከአንድ የእግዚአብሔር አገልጋይ የሚጠበቅ ሃላፊነት ነው፡፡ እንዲሁ ሌሎች እንዲፀልዩ ማበረታታት ከእግዚአብሔር
ሰው እንደመፍትሄ የሚጠበቅ ነው፡፡
ነገር ግን ቪድዮ እየቀረፃችሁ በሚያቃጥል አስፋልት
ላይ አስቀምጣችሁ ግረፉ ብሎ ወጣቱን ማነሳሳት መፅሃፍ ቅዱሳዊም አይደለም እንዲሁም ህጋዊም አይደለም፡፡
ይህ ሰዎችን ለደቦ ፍርድ የሚያበረታታ አደገኛ
ምክር ነው፡፡ በፖለቲካ ውስጥ አይተን የምንፀየፈውን የደቦ ፍርድ ለዚህ መፍትሄነት መጠቀም ንስሃ የሚያስፈልገው ስህተት ነው፡፡
ይህ ወጣቶችን ማነሳሳት በፍርድ ቤት ሊያስፈርድ
የሚችል በደል ነው፡፡ አንድ ቀን ልጆች እንደተባለው አድርገው ተከስሰው ፍርድ ቤት ቢቀርቡና መሪያችን ኢዩ ጩፋ ነው ያዘዘን ቢሉ
የሚያሳስር እና የሚያስፈርድ ወንጀል ነው፡፡
በኢትዮጲያ ህገ መንግስት መሰረት ሰው በፍርድ
ቤት ተከስሶ ተከራክሮ በነፃ ፍርድ ቤት ጥፋተኛ እስካልተባለ ድረስ ንፁህ ነው፡፡ በኢትዮጲያ ህግ የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትን መፈፀም
ወንጀል ነው፡፡ ተጠርጣሪን ለፍርድ አቅርቦ በፍርድ ቤት ተመጣጣኝ ቅጣት እንዲያገኝ ከማድረግ ባለፈ ራስ ጠርጥሮ ፣ ራስ ፈርዶ ፣
ራስ ፍርድን ማስፈፀም የህግ የበላይነትን የሚቃወም የደቦ ፍርድ ነው፡፡
መፅሃፍ ቅዱስ ሙሉ ነው፡፡ መፅሃፍ ቅዱስ ስለሁሉም
ነገር ሙሉ መልስ አለው፡፡ ወጣቶችን ቪድዮ እየቀረፃችሁ ግረፉ ከማለት ይልቅ የእግዚአብሔርን የወንድን እና የሴትን አፈጣጠር ከቃሉ
በማስረዳት ህዝቡን ማስተማር ይገባ ነበር፡፡ ወጣቶችን በግብታዊነት ለደቦ ፍርድ ከማነሳት ይልቅ የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት በእግዚአብሔር
የአፈጣጠር ተፈጥሮ ጋር አብሮ የማይሄድ አገደኛ ሃጢያት መሆኑን ማሳየት የአንድ የቤተክርስትያን መሪ ሃላፊነት ነው፡፡
ሌሎች የቤተክርስትያን መሪዎች ሁሉ ከዚህ ስህተት
ተምራችሁ መፅሃፍ ቅዱስ ስለተመሳይ ፆታ አደገኝነት የሚናገረውን በቃሉ ለህዝባችሁ አስተምሩ፡፡
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ
Abiy Wakuma Dinsa
#ኢየሱስ #ጌታ
#ጋብቻ #ፍቅር
#ተቃራኒፆታ #ወንድ
#ሴት #ወንድእናሴት
#ተመሳሳይፆታ #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #ትዳር
No comments:
Post a Comment