Popular Posts

Tuesday, August 22, 2023

ወንጌልን የሚሰብኩ ከወንጌል ቀለብ እንዲቀበሉ ጌታ ደንግጎአል

 

በመቅደስ ነገር የሚያገለግሉ ከመቅደስ የሆነውን ነገርን እንዲመገቡ፥ በመሠዊያውም የሚጸኑ ከመሠዊያው እንዲካፈሉ አታውቁምን? እንዲሁ ደግሞ ወንጌልን የሚሰብኩ ከወንጌል ቀለብ እንዲቀበሉ ጌታ ደንግጎአል። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 9፡13-14

በወንጌል ስራ ላይ ለማተኮር አብዛኛው ጊዜያቸውን ለወንጌል ስራ የሚሰጡ አገልጋዮች በምድር ላይ ለመኖር የሚያስፈልጋቸውን ገንዘብ የሚያገኙት የወንጌል ማህበርተኞች ከሚያዋጡት መዋጮ ነው፡፡

እውነት ነው ሁሉም ሰው ወንጌልን ይሰራል፡፡ ነገር ግን ሁሉም ሰው አብዛኛው ጊዜውን ለወንጌል ስራ አይሰጥም፡፡

አብዛኛው ጊዜያቸውን ለወንጌል ስራ የሚሰጡ አገልጋዮች ለኑሮ የሚያስፈልጋቸውን ገንዘብ የሚያገኙት በስራ ቦታ ወጥተው ከሚሰሩት የወንጌል ሰራተኞች መዋጮ ነው፡፡

ሌሎች በስራ ቦታቸው ገንዘብ ሰርተው መጥተው ለወንጌል ሰባኪው ገንዘብ ሲሰጡ ለወንጌል ሰባኪ መልካም ስሜት ላይሰጠው ይችላል፡፡

ነገር ግን ጌታ የደነገገው የጌታ አሰራር ይህ ነው፡፡ የወንጌል ሰባኪው በስራ ቦታ ሰርቶ ገንዘብን ማግኘት ይችላል፡፡ የወንጌል ሰባኪው በስራ ቦታ ሰርቶ የራሱን ገንዘብ ማግኘት ሲችል ሌሎች የሰሩትን ገንዘብ አምጥተው ሲሰጡት ቢሰማውም የእግዚአብሔርን አሰራር ማክበር ግን አለበት፡፡

በዋነኝነት ወንጌልን የሚሰብክ ሰው ከስሜቱ ይልቅ  የእግዚአብሔርን አሰራር በትህትና ማክበር አለበት፡፡ በዋነኝነት ወንጌልን የሚሰብክ አገልጋይ የእኔነት ክብሩን ዋጥ አድርጎ ጌታ የደነገገውን አሰራር መከተል ይኖርበታል፡፡

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

#ኢየሱስ #ጌታ #ገንዘብ #ቀለብ #ወንጌል #ኑሮ #ስጡ #ቤተክርስቲያን #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #ገቢ


No comments:

Post a Comment