በመልካም
የሚያስተዳድሩ ሽማግሌዎች፥ ይልቁንም በመስበክና በማስተማር የሚደክሙት፥ እጥፍ ክብር ይገባቸዋል። መጽሐፍ፦ የሚያበራየውን በሬ አፉን
አትሰር፥ ደግሞ፦ ለሠራተኛ ደመወዙ ይገባዋል ይላልና። 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 5:17-18
በኢየሱስ
ክርስቶስ አዳኝነት ያመንን ሁላችን የመጀመሪያው ሙያችን ወንጌል ነው፡፡
ክህንነት ሁላችንም የምንሰራው የመጀመሪያው ጥሪያችን ነው፡፡ እንዲሁም የአለም ብርሃን እና የምድር ጨው ለመሆን የምንሰማራበት ሙያ
ደግሞ ይኖረናል፡፡
በዋነኝነት
ግን የምናገለግለው ጌታ ክርስቶስን ነው የርስትም ብድራት የምንቀበለው ከእርሱ ነው፡፡
ባሪያዎች
ሆይ፥ በቅን ልብ ጌታን እየፈራችሁ እንጂ፥ ለሰው ደስ እንደምታሰኙ ለታይታ የምትገዙ ሳትሆኑ፥ በሥጋ ጌቶቻችሁ ለሆኑ በሁሉ ታዘዙ።
ለሰው ሳይሆን ለጌታ እንደምታደርጉ፥ የምታደርጉትን ሁሉ በትጋት አድርጉት፥ ከጌታ የርስትን ብድራት እንድትቀበሉ ታውቃላችሁና፤ የምታገለግሉት
ጌታ ክርስቶስ ነውና።ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3፡22-24
ወንጌል
በመስበክ እና በማስተማር የሚተጉት አገልጋዮች ግን እንደ ሌሎቹ ክርስቲያኖች ከሌላ ሙያ ገንዘብ አያገኙም፡፡ ታዲያ በመስበክ እና
በማስተማር የሚደክሙት ለኑሮ በሚያስፈልጋቸው የሚንከባከቡት በተለያየ ሙያ ላይ ተሰማርተው ገንዘብ የሚያገኙ ቅዱሳን ናቸው፡፡
ይህ
መፅሃፍ ቅዱሳዊ መርህ ነው፡፡ አብዛኛው ጊዜያቸውን ለወንጌል ለሚሰጡት አገልጋዮች ገንዘብን መስጠት ሊደረግ የሚገባ ትክክለኛ ነገር
ነው፡፡ እንዲሁም ወንጌልን የሚሰሩ አገልጋዮች ደግሞ ካለ መሸማቀቅ እና ካለመሳቀቅ ከሌሎች ቅዱሳን ገንዘብን ሲቀበሉ ይገባቸዋል፡፡
አቢይ
ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma
Dinsa
#ኢየሱስ
#ጌታ #ገንዘብ #ቀለብ #ወንጌል #ኑሮ #ስጡ #ቤተክርስቲያን #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #ገቢ
No comments:
Post a Comment