በእግዚአብሔር ቃል ከስር ጀምረን ካስተማርናቸው
እኛን እንደሚቀፈን ሁሉ እነርሱንም ይቀፋቸዋል፡፡
መፍትሄው መፍራት አይደለም፡፡ መፍትሄው ማስታጠቅ
ነው፡፡ መፍትሄው እኛ አጠገባቸው በሌለን ጊዜ ውሳኔ የሚወስኑበትን ጥበብ ማካፈል ነው፡፡
መፍትሄው ልጆቻችን አያውቁም አይረዱም በማለት
"አትያዝ፥ አትቅመስ፥ አትንካ" በሚል ትእዛዝ መምራት ሳይሆን እኛ በሌለን ጊዜ እንዴት ውሳኔን እንዲወስኑ የውሳኔውን
መሳሪያውን መስጠት ነው፡፡ በየጊዜው ለልጆቻችን ውሳኔን ሰርቶ መስጠት ሳይሆን የሚሰሩበትን መሳሪያ ሰጥቶ እንዴት እንደሚወስኑ በእውቀት
ማስታጠቅ ነው፡፡
ልጆች አምነው ካልተቀበሉት አይሰራባቸውም፡፡
ታዲያ እንደ መረዳት አቅማቸው በትጋት ማስተማር እንጂ ብርር ብሎ እንደሚገባባቸው ጭራቅ አድርጎ መፍራት መፍትሄ አይሆንም፡፡
ልጅን በሚሄድበት መንገድ ምራው፥ በሸመገለም
ጊዜ ከእርሱ ፈቀቅ አይልም። መጽሐፈ ምሳሌ 22፡6
ስናስተምር ደግሞ ሙሉውን የእግዚአብሔርን እቅድ
ማስተማር አለብን፡፡ ስለተመሳሳይ ፆታ ብቻ ብናስጠነቅቃቸው ሙሉ አይሆንም፡፡ የእግዚአብሔር ቃል ባልጠጋ ነው፡፡ ሙሉውን የፆታ ግንኙነት
እግዚአብሔር ቃል ማስተማር ይኖርብናል፡፡
ሃጢያት መጨረሻ የለውም፡፡ ብዙ እና ተለዋዋጭ
ስለሆነው ስለሃጢያቱ ከማስተማር ይልቅ የእግዚአብሔርን ቃል ማስተማር በማንኛውም ጊዜ እውተኛውን ከሃሰተኛው በቀላሉ እንዲለዩ ይረዳቸዋል፡፡
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ
Abiy Wakuma Dinsa
#ኢየሱስ #ጌታ #ጋብቻ
#ፍቅር #ተቃራኒፆታ
#ወንድ #ሴት
#ወንድእናሴት #ተመሳሳይፆታ #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር
#ትዳር
#ግብረሰዶም #ግብረሰዶማዊነት
No comments:
Post a Comment