አሁንስ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ በፍጹም ልባችሁ፥ በጾምም፥ በልቅሶና በዋይታ ወደ እኔ ተመለሱ። ልባችሁን እንጂ ልብሳችሁን አትቅደዱ፤ አምላካችሁም እግዚአብሔር ቸርና መሐሪ፥ ቍጣው የዘገየ፥ ምሕረቱም የበዛ፥ ለክፋትም የተጸጸተ ነውና ወደ እርሱ ተመለሱ። ትንቢተ ኢዮኤል 2፡12-13
ንስሐ
ማልቀስ አይደለም፡፡ ንስሐ መፀፀት አይደለም፡፡ ንስሐ ስለሃጢያታችን ራሳችንን መቅጣት አይደለም፡፡ ንስሐ ስለሃጢያታችን ራሳችንን ማጎሳቆል አይደለም፡፡
ክፉ ሰው መንገዱን በደለኛም አሳቡን
ይተው፤ ወደ እግዚአብሔርም ይመለስ እርሱም ይምረዋል፥ ይቅርታውም ብዙ ነውና ወደ አምላካችን ይመለስ። ትንቢተ ኢሳይያስ 55፡7
ንስሐ
ሃሳብን መቀየር ነው፡፡ ንስሐ መንገድን መቀየር ነው፡፡ ሰው ባያለቅስም እንኳን የተሳተ መንገዱን መንገዱን እስከቀየረ ድረስ የእግዚአብሔርብ
ልብ ደስ ያሰኛል፡፡
አሁንም
ሁላችሁ ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፥ መንገዳችሁንና ሥራችሁንም አቅኑ ብለህ ተናገራቸው። ትንቢተ ኤርምያስ 18፡11
ንስሐ
ያደርጉት የነበረው ነገር የተሳተ እንደሆነ ሲረዱ መመለስ ማለት ነው፡፡ ንስሐ ማለት መደረግ የነበረበት ነገር እንዳልተደረገ ሲረዱ
ለማድረግ መወሰን ማለት ነው፡፡
#ኢየሱስ
#ጌታ #ንስሐ
#አእምሮንማደስ #አሳብንመቀየር #መንገድንመቀየር #በረከት #ቤተክርስቲያን
#መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #ክርስትና
No comments:
Post a Comment