Popular Posts

Tuesday, August 29, 2023

ወንጌልን የሚሰብኩ ከወንጌል ቀለብ እንዲቀበሉ ጌታ ደንግጎአል ክፍል 8

 

አብዛኛው ወንጌልን የሚሰሩ አብዛኛው አገልጋዮች ከእግዚአብሔር ነው አንጂ በሰው አይከፈላቸውም፡፡ አብዛኛዎቹ የወንጌል አገልጋዮች በስጦታቸው ብቻ ሳይሆን በገንዘባቸውም ጌታን በደስታ ያገለግላሉ፡፡

ለምሳሌ በዘማሪነት የሚያገለግሉ አገልጋዮች እግዚአብሔር ከሰጣቸው ስጦታ በተጨማሪ ለስልጠና ተጨማሪ የትራንስፖርት ወጪ አውጥተው ጌታን ያገለግላሉ፡፡ አብዛኛዎቹ መክፈል ችለው በደስታ በገንዘባቸውም ጭምር ጌታን ያገለግላሉ፡፡ ቤተክርስትያን አቅሙ ኖሮዋት በተለይ መክፈል የማይችሉትን ብትከፍል ለቤተክርስቲያንም በረከት ነው፡፡ ምክኒያቱም ጊዜያቸውን ፣ ጉልበታቸውን ፣ ስጦታቸውን ከመስጠታቸው በተጨማሪ ገንዘባቸውን መስጠታቸው ተጨማሪ መስዋእትነት ነው፡፡

ሳይከፈላቸው የሚያገለግሉት የወንጌል አገልጋዮች አገልግሎት እጅግ እየሰፋ ይመጣል፡፡ አገልግሎቱ እየሰፋ በመጣ መጠን አገልግሎታቸው ተጨማሪ ጊዜያቸውን እየፈለገ መምጣት ይጀምራል፡፡ ታዲያ አገልግሎታቸው ይሰፋና በትርፍ ጊዜታቸው ብቻ ማገልገል የማይችሉበት ሁኔታ ላይ ይደርሳሉ፡፡ በትርፍ ጊዜ ብቻ ማገልገል የማይቸሉበት ደረጃ ላይ ሲደርሱ በሌላ ሙያ የሚሰሩትን ስራ ጥለው መውጣት ግድ ይላቸዋል፡፡ ታዲያ ቤተክርስትያን ለኑሮ የሚያስፈልጋቸውን ወጪ በመሸፈን በተጨማሪ ጊዜያቸው በወንጌሉ ላይ እንዲያተኩሩ ትጠይቃቸዋለች፡፡

አገልጋዮቹም በእግዚአብሔር በመታመን በሌላ ሙያ የሚሰሩትን ስራቸውን ትተው በአብዛኛው ጊዜያቸው ወንጌልን ለማገልገል እና በወንጌል ለመኖር ይወስናሉ፡፡

ሁላችንም የወንጌል አገልጋዮች ነን፡፡ የወንጌሉም አገልጋዮች በትርፍ ጊዜያቸው ብቻ ለሚሰራ አገልግሎት ወጪያቸውን እንድትሸፍን ቤተክርስቲያን ላይ ሊከብዱባት አይገባም፡፡

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

#ኢየሱስ #ጌታ #ገንዘብ #ቀለብ #ወንጌል #ኑሮ #ስጡ #ቤተክርስቲያን #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #ገቢ


No comments:

Post a Comment