ባለፉት
ተከታታይ ፅሁፎች ልጆቻችንን ከተመሳይ ፆታ
ግንኙነት ተግዳሮት እንዴት
መጠበቅ እንዳለብን
የተለያዩ ነገሮችን አንስተናል፡፡
ከአጠቃላይ
የስጋ ስራዎች ተግዳሮቶች አንፃር የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ተግዳሮት ጥቂት ነው፡፡ ልጆቻችን በአጠቃላይ በስጋ ስራዎች ተግዳሮት
ስር ናቸው፡፡ ልጆቻችን ይበልጥ የሚፈተኑት በሌሎች የስጋ ስራዎች ነው፡፡
ልጆቻችን
በየጊዜው በሚገጥማቸው በእያንዳንዱ ተግዳሮቶች ላይ ከማተኮር ይልቅ በአጠቃላይ እንዴት በእግዚአብሔር መንገድ እንደሚኖሩ ከስር መሰረቱ
ማስተማር የተሻለ መፍትሄ ነው፡፡
የሰይጣን
ተግዳሮት በተመሳይ ፆታ ግንኙነት ላይ ብቻ አያበቃም፡፡ የሰይጣን ተግዳሮት ዘርፈ ብዙ ነው፡፡ የሃጢያት አይነቱ ብዙ ነው፡፡ ይህንን
ዘርፈ ብዙ ተግዳሮት የምንቋቋመው ምንም ሳይመጣ በፊት አስቀድመን ከልጅነታቸው በእግዚአብሔር ቃል እውቀት በማስታጠቅ ብቻ ነው፡፡
የእውነትን
ቃል በቅንነት የሚናገር የማያሳፍርም ሠራተኛ ሆነህ፥ የተፈተነውን ራስህን ለእግዚአብሔር ልታቀርብ ትጋ። 2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2፡15
ልጆቻችንን
ለማስተማር ደግሞ እኛ ራሳችን ጊዜ ወስደን የእግዚአብሄርን ቃል ለመማር መትጋት አለብን፡፡ ልጆቻችንን ጭራቅ ይበላችሁዋል ወደዚያ
እንዳትሄዱ በሚል አካሄድ አንመልሳቸውም፡፡ ይልቁንም እኛ ራሳችን የእግዚአብሔርን ቃል በማጥናት ራሳችንን አስቀድመን ማስታጠቅ ይጠበቅብናል፡፡
በእናንተ
ስላለ ተስፋ ምክንያትን ለሚጠይቁአችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር የተዘጋጃችሁ ሁኑ፥ 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 3፡15
ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ ይህንን ተፈጥሮአዊ ባልሆነ
ነገር ራሳቸውን እንዲያጎሳቁሉ የሚያደርጋቸው የክፉ ሃይል እንዳለ ተረድተን ፀንተን በእምነት መቃወም ይኖርብናል፡፡ በክፉው የዲያቢሎስ
አለም የሚበረታታውን ይህን ተግዳሮት በስጋ ተቃውሞ ለመግታት መሞከር ሞኝነት ነው፡፡ ያለንን የእግዚአብሔርን ቃል በማስተማር እንዋጋዋለን
እንዲሁም በተሰጠን በልጅነት ስልጣናችን በክርስቶስ የመስቀል ስራ ስልጣኑ የተሻረውን የዲያቢሎስን ስራውን እናፈርሳለን፡፡
የጦር ዕቃችን ሥጋዊ አይደለምና፥ ምሽግን ለመስበር ግን በእግዚአብሔር ፊት ብርቱ ነው፤ የሰውንም አሳብ በእግዚአብሔርም እውቀት ላይ የሚነሣውን ከፍ ያለውን ነገር ሁሉ እናፈርሳለን ለክርስቶስም ለመታዘዝ አእምሮን ሁሉ እንማርካለን፥ 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 10፡4-5
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ
Abiy Wakuma Dinsa
#ኢየሱስ #ጌታ #ጋብቻ
#ፍቅር #ተቃራኒፆታ
#ወንድ #ሴት
#ወንድእናሴት #ተመሳሳይፆታ #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር
#ትዳር
#ግብረሰዶም #ግብረሰዶማዊነት
No comments:
Post a Comment