በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል . . . እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን። ትንቢተ ኢሳይያስ 53፡4-5
ኢየሱስ በመስቀል ላይ ሃጢያታችንን ወስዶ ፅድቅን እንደሰጠን ሁሉ
ኢየሱስ በመገረፉ
በሽታችንን ወስዶ ፈውስን ሰጥቶናል፡፡
መስቀል የእኛ የሆነውን በእርሱ የእርሱ የሆነውን በእኛ የመለዋወጫ ቦታ
ነው፡፡ ኢየሱስ
በመስቀል ላይ
የእኛን ድካም
ወስዶ ብርታትን
ሰጥቶናል፡፡
ኢየሱስ በመስቀል ላይ ሙሉ ዋጋ
የከፈለው እና
ተፈፀመ ያለው
ከሃጢያት ድነን
በስጋ እንድንደክም
አይደለም፡፡ ኢየሱስ ለሃጢያታችን ዋጋ ሲከፍል ለነፍሳችን መዳን እና ለስጋችን
ፈውስ ሙሉ ዋጋ ለመክፈል ነበር፡፡
ከእግዚአብሔር ጋር ለመታረቅ እና
የእግዚአብሔር ልጅ
ለመሆን ነፍሳችን
ከሃጢያት እስራት
ነፃ መሆን
እንዳለባት ሁሉ
በምድር ላይ
በብርታት ጌታን
እንድንከተለው እና
እንዳገለግለው ከበሽታ
እና ከደዌ መፈታት ነበረብን፡፡ እግዚአብሔርን እንዳናገለግለው የሚያደርገን
ደዌ እና ህመም መፍትሄ ባይገኝለት ኖሮ ነፍሳችን ከሃጢያት ድኖ ስጋችን በህማም እና በደዌ የጠላት መጫወቻ ይሆን ነበር፡፡ እግዚአብሔር
ለነፍሳችን መዳን መፍትሄ ሰጥቶ ስጋችንን ባይፈወስ ኖሮ ልክ እንደዳንን ወደመንግስተ ሰማይ ካልሄድን በስተቀር በምድር ላይ በብርታት
ጌታን ማገልግል አንችልም ነበር፡፡
በመሸም ጊዜ አጋንንት
ያደረባቸውን ብዙዎችን
ወደ እርሱ
አመጡ፤ በነቢዩ
በኢሳይያስ፦ እርሱ
ድካማችንን ተቀበለ
ደዌያችንንም ተሸከመ
የተባለው ይፈጸም
ዘንድ፥ መናፍስትን
በቃሉ አወጣ፥
የታመሙትንም ሁሉ
ፈወሰ።የማቴዎስ ወንጌል 8፡16-17
የነፍሳችን መዳን የመቤዠታችን
ክፍል እንደሆነ
ሁሉ የስጋ
ፈውስ የመቤዠታችን
አንዱ አካል
ነው፡፡
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ
Abiy Wakuma Dinsa
#ኢየሱስ #ጌታ #ህማም
#ደዌ #ወንጌል
#ፈውስ #ጤንነት
#ቤተክርስቲያን #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #መስቀል
#በመገረፉ #ቁስል #ተፈወሳችሁ
No comments:
Post a Comment