Popular Posts

Sunday, August 13, 2023

ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም

 

ኢየሱስም መልሶ፦ እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም አለው። የዮሐንስ ወንጌል 33

ሰው ከእናት እና ከአባቱ በመወለድ ወደዚህ ምድር ውስጥ ይገባል፡፡ ወደዚህ ምድር ለመግባት ከአባት እና ከእናት መወለድ የግዴታ ነው፡፡ ከእናት እና ከአባት ያልተወለደ ሰው ወደዚህ ምድር መግባት በፍፁም አይችልም፡፡ ከአባት እና ከእናት ከመወለድ ውጭ ወደዚህ ምድር የመግቢያ ሌላ ምንም መንገድ የለም፡፡

ሰው ወደዚህ ምድር ለመግባት ከሰው መወለድ እንዳስፈለገው ሁሉ ሰው ወደ እግዚአብሄር መንግስት ለመግባት ከእግዚአብሔር መወለድ አለበት፡፡

ኢየሱስም መለሰ፥ እንዲህ ሲል፦ እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም። የዮሐንስ ወንጌል 3፡5

ሰው ከሰው መወለዱ ብቻ ከእግዚአብሔር ለመወለድ ብቁ አያደርገውም፡፡ ሰው ለሃጢያታችን በመስቀል ላይ የተሰቀለውን ኢየሱስ ክርስቶስን ስለእርሱ ሃጢያት እንደተለት እና ከሙታን እንደተነሳ በማመን ዳግመኛ መወለድ ያስፈልገዋል፡፡

ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤ ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናልና። ወደ ሮሜ ሰዎች 10፡9-10


No comments:

Post a Comment