Popular Posts

Monday, August 7, 2023

ልጆቻችንን ከተመሳይ ፆታ ተግዳሮት መጠበቅ ክፍል 1

በክፉው የተያዘው አለም ከእኛ ይልቅ ልጆቻችንን በሃጢያት ለማጥመድ ይፈልጋል፡፡ እኛ ያደግነው በእምነት እንደተለወጥን እኛን በቀላሉ ለመለወጥ ጊዜው እንደረፈደበት ያስባል፡፡ ታዲያ የአለም ስርአት በሙሉ ሃይሉ የሚመጣው ልጆቻችንን ለመንጠቅ ነው፡፡ 

ከእግዚአብሔር እንደ ሆንን ዓለምም በሞላው በክፉው እንደ ተያዘ እናውቃለን። 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 5፡19

ልጆቻችን ደግሞ እንደ ንፁህ ወረቀት ናቸው፡፡ ታዲያ ውድድሩ ቀድሞ በመፃፍ ነው፡፡ አለም ቀድማ ከፃፈች እኛ ለመፃፍ መጀመሪያ የተፃፈውን መሰረዝ ከዚያም አዲስ መፃፍ ስለሚጠበቅብን ስራችንን ይበልጥ አስቸጋሪ ያደርገዋል፡፡

ልጅን በሚሄድበት መንገድ ምራው፥ በሸመገለም ጊዜ ከእርሱ ፈቀቅ አይልም። መጽሐፈ ምሳሌ 22፡6

አለም የምትፈራው ደግሞ የእግዚአብሔርን የጥንቱን እቅድ ያለንን እኛን የመፅሃፍ ቅዱስ ሰዎች ነው፡፡አለም እኛን እንደምትፈራ ሌሎችን የህብረተሰብ ክፍሎች አትፈራም፡፡ እኛ ሙሉ የእግዚአብሔር የአፈጣጠር ንድፍ በመፅሃፍ ቅዱስ ተፅፎ አለን፡፡

ሌሎቹ የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ተፈጥሮአዊ ስላልሆነ ስለማይዋጥላቸው ብቻ በባህላችን የተከለከለ ነው ብለው ሊቃወሙት ይችላሉ፡፡

እኛ ግን ሙሉውን የእግዚአብሔርን አፈጣጠር ንድፍ በመፅሃፍ ቅዱስ እንረዳለን፡፡

የአዳም የትውልዱ መጽሐፍ ይህ ነው። እግዚአብሔር አዳምን በፈጠረ ቀን በእግዚአብሔር ምሳሌ አደረገው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው፥ ባረካቸውም። ስማቸውንም በፈጠረበት ቀን አዳም ብሎ ጠራቸው። ኦሪት ዘፍጥረት 5፡1-2

ልጆቻችንን በሚሄዱበት መንገድ ለመምራት እንደእኛ በመኝሃፍ ቅዱስ ውስጥ ሙሉ እውቀት የቀረበለት ማንም ሰው የለም፡፡

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

#ኢየሱስ #ጌታ #ጋብቻ #ፍቅር #ተቃራኒፆታ #ወንድ #ሴት #ወንድእናሴት #ተመሳሳይፆታ #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #ትዳር  #ግብረሰዶም #ግብረሰዶማዊነት


 

No comments:

Post a Comment