Popular Posts

Thursday, August 24, 2023

ወንጌልን የሚሰብኩ ከወንጌል ቀለብ እንዲቀበሉ ጌታ ደንግጎአል ክፍል 3

 

እንዲሁ ሰው እኛን እንደ ክርስቶስ ሎሌዎችና እንደ እግዚአብሔር ምሥጢር መጋቢዎች ይቍጠረን። እንደዚህም ሲሆን፥ በመጋቢዎች ዘንድ የታመነ ሆኖ መገኘት ይፈለጋል። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 4፡1-2

ወንጌልን የሚሰብኩት አገልጋዮችን የኑሮ ወጪ የመሸፈን ሃላፊነት ያለበት ወንጌል የሚሰበክለት እና በእግዚአብሔር ቃል እውቀት የሚመገበው ህዝብ ነው፡፡

ነገር ግን በቃሉ መጋቢዎች ዘንድ ለቃሉ እና ለፀሎት ራስን ለመለየት የታመነ ሆኖ መገኘት ይጠይቃል፡፡ መጋቢዎች ቃሉን ለማንበብ ፣ ለማጥናት ፣ ለማሰላሰል እንዲሁም ለህዝቡ በመፀለይ አብዛኛውን ጊዜያቸውን ሊሰጡ ይገባቸዋል፡፡

መጋቢዎች የእግዚአብሔርን ፊት ለመፈለግ ከእግዚአብሔር የሆነን መልእክት ለማምጣት መንጋውን የለመለመ ሳር ለመመገብ በእግዚአብሔር ፊት መቆየት አለባቸው፡፡

መጋቢዎች በሌሎች ስራዎች ላይ ከተሰማሩ ክርስቲያኖች እኩል በተለያየ በወንጌል ባለሆነ ነገር ተጠምደው ቆይተው ህዝቡን በሚገባ ሊመግቡት በፍጹም አይችሉም፡፡

መጋቢዎች ሌላ ስራ እንዳይሰሩ የተፈለገበት ምክኒያት ራሳቸውን ለእግዚአብሔር ቃል እና ለፀሎት እንዲለዩ ነው፡፡ መጋቢዎች ራሳቸው ወጥተው ከመስራት ይልቅ ሌሎች ሰርተው ለእግዚአብሔር ቤት በሰጡት ገንዘብ እንዲኖሩ ያስፈለገበት ምክኒያት የእግዚአብሔርን ፊት ለመፈለግ አብዛኛውን ጊዜያቸውን እንዲሰጡ ነው፡፡

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

#ኢየሱስ #ጌታ #ገንዘብ #ቀለብ #ወንጌል #ኑሮ #ስጡ #ቤተክርስቲያን #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #ገቢ



No comments:

Post a Comment