Popular Posts

Friday, August 11, 2023

ልጆቻችንን ከተመሳይ ፆታ ተግዳሮት መጠበቅ ክፍል 4

ሰይጣን ልጆቻችንን ለመንጠቅ አስፍስፎ እየጠበቀ ነው፡፡ ሰይጣን በፊልም በመፅሃፍ የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትን የተለመደ ለማድረግ ብዙ ይጥራል፡፡

ነገር ግን የተለመደ ነገር እንዳይደለ ማሳየት ልጆቻችንን ይጠብቃቸዋል፡፡

የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ተፈጥሮአዊ እንዳይደለ ከመፅሃፍ ቅዱስ በተጨማሪ ተፈጥሮ እንኳን ያስተምረናል፡፡ አንዳንድ ነገር ትክክል ነው አይደለም የሚል ጥያቄ ውስጥ ብንገባ ተፈጥሮን ብቻ በመመልከት ወደ እውነት ያደርሰናል፡፡

የሰው ተፈጥሮ የተነደፈው ለተቃራኒ ፆታ ግንኙነት ነው፡፡ የሰውን መላውን የሰውነት ክፍል ስንመለከት ለተፈጥሮአዊው ለተቃራኒ ፆታ ግንኙነት እንደተፈጠረ እንረዳለን፡፡ የሰውን እያንዳንዱን የባዮሎጂ ስርአት ስንመለከት ለተቃራኒ ፆታ ግንኙነት ታስቦ እና ታቅዶ የተሰራ መሆኑን እንመለከታለን፡፡ የሰውን እያንዳንዱን ሆርሞን እና ኬሚካል ስንመለከት ለተቃራኒ ፆታ ታስቦ እንደተሰራ ተፈጥሮ እንኳን ያሳያል፡፡ የሰውን የስነ ተዋልዶ ስርአት ስንመለከት ለተቃራኒ ፆታ ግንኙነት ታስቦ እንደሆነ ተፈጥሮ ያስተምረናል፡፡

ተፈጥሮ እንኳ አያስተምራችሁምን? 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11፡14

ከተመሳሳይ ፆታ ጋር ግንኙነት የሚያደርግ ምንም አይነት ፍጥረት የለም፡፡

ሰው በአመፅ በተፈጥሮ ላይ ተነስቶ አይሳካለትም፡፡ ሰው ሊያደርገው የሚችለው የተሻለ ነገር ቢያንስ ቢያንስ ተፈጥሮን መከተል ነው፡፡

ሰው የእግዚአብሄር ቃል ስለተቃራኒ ፆታ የሚለው ሰምቶ ባያውቅ እንኳን ተፈጥሮን መስማት አለበት እንጂ  ከተፈጥሮ ተቃራኒ በመሄድ መጥፋት የለበትም፡፡

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

#ኢየሱስ #ጌታ #ጋብቻ #ፍቅር #ተቃራኒፆታ #ወንድ #ሴት #ወንድእናሴት #ተመሳሳይፆታ #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #ትዳር  #ግብረሰዶም #ግብረሰዶማዊነት


 

No comments:

Post a Comment