Popular Posts

Wednesday, August 2, 2023

አስቀድማችሁ ከፈሪሳውያን እርሾ ተጠበቁ! ክፍል 5

 

አስቀድማችሁ ከፈሪሳውያን እርሾ ተጠበቁ፥ እርሱም ግብዝነት ነው።የሉቃስ ወንጌል 121

ፈሪሳዊነት እያንዳንዳችንን እለት በእለት የሚፈትነን አመለካከት እንጂ ሰው አይደለም፡፡

ፈሪሳዊነት ማለት መንፈሳዊ ነገርን ለራስ ሳይረዱ እና ሳይተገብሩ ለሌላው ማስተማር እና ስለመንፈሳዊነት መመካት ማለት ነው፡፡ ፈሪሳዊነት በውጭ መንፈሳዊ መምሰል በውስጥ ግን መንፈሳዊ አለመሆን ነው፡፡ ፈሪሳዊነት ለውጭ እይታ ብቻ እንጂ ለእውነተኛው መንፈሳዊነት ዋጋ አለመስጠት ነው፡፡

በሥጋ መልካም ሆነው ሊታዩ የሚወዱ ሁሉ እንድትገረዙ ግድ አሉአችሁ፥ ነገር ግን ስለ ክርስቶስ መስቀል እንዳይሰደዱ ብቻ ነው። በሥጋችሁ እንዲመኩ ልትገረዙ ይወዳሉ እንጂ የተገረዙቱ ራሳቸው እንኳ ሕግን አይጠብቁም። ወደ ገላትያ ሰዎች 6፡12-13

ፈሪሳዊነት ማለት ለሰው እይታ እንጂ ለእግዚአብሔር አለመኖር ማለት ነው፡፡ ፈሪሳዊነት ከሰው ክብር ለማግኘት መጨነቅ ብቻ እንጂ ከእግዚአብሔር የሚመጣውን ክብር አለመፈለግ ነው፡፡

እናንተ እርስ በርሳችሁ ክብር የምትቀባበሉ ከአንዱም ከእግዚአብሔር ያለውን ክብር የማትፈልጉ፥ እንዴት ልታምኑ ትችላላችሁ? የዮሃንስ ወንጌል 5፡44

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

#ኢየሱስ #ጌታ #ፈሪሳውያን #ግብዝነት #የአምልኮትመልክ # #ጻፎች #ቤተክርስቲያን #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #ሰዱቃውያን


No comments:

Post a Comment