Popular Posts

Saturday, August 26, 2023

ወንጌልን የሚሰብኩ ከወንጌል ቀለብ እንዲቀበሉ ጌታ ደንግጎአል ክፍል 5

 

ወንጌልን የሚሰብኩ ከወንጌል ቀለብ እንዲቀበሉ ጌታ ደንግጎአል ክፍል 5

ለሌዋውያንም እድል ፈንታቸው እንዳልተሰጠ፥ የሚያገለግሉትም ሌዋውያንና መዘምራን እያንዳንዱ ወደ እርሻው እንደ ሄዱ ተመለከትሁ። መጽሐፈ ነህምያ 13፡10

በብሉይ ኪዳን የሌዋዊያን እድል ፈንታቸው ከህዝቡ የሚሰበሰበው መዋጮ ነበር፡፡ ህዝቡ ሃላፊነቱን ስላልተወጣ ሌዋዊያኑ የእግዚአብሔር ቤት ስራ ትተው ወደ እርሻ ስራ ሄደው ነበር፡፡ 

በአዲሱም ኪዳን የእግዚአብሔር ቃል እንዲያሸንፍ ፣ የእግዚአብሔር ህዝብ በሚገባ እንዲመገብ እና እንዲጠበቅ  የእግዚአብሔር ህዝብ ለነፍሱ የሚተጉትን የወንጌል ሰራተኞችን የመንከባከብ ሃላፊነት አለበት፡፡ 

አብዛኛው ጊዜያቸውን በወንጌል ስራ ላይ የሚያሳልፉትን በሚያስፈልጋቸው ነገር መንከባከብ ለቤተክርስትያን ፣ ለእግዚአብሔር አሰራር ፣ ለወንጌል እና ለእግዚአብሔር መንግስት ያለንን አክብሮት ያሳያል፡፡

በቤተክርስቲያን የወንጌል ሰራተኞች የሚደረግልንን አገልግሎት ካከበርን እና ዋጋ ከሰጠን ለእነርሱ የእለት ተእለት ወጭ መሸፈኛ የሚሆንን ነገር መስጠት ትልቅ ነገር አይሆንብንም፡፡

እኛ መንፈሳዊን ነገር የዘራንላችሁ ከሆንን የእናንተን የሥጋዊን ነገር እኛ ብናጭድ ትልቅ ነገር ነውን? 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 9፡11

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

#ኢየሱስ #ጌታ #ገንዘብ #ቀለብ #ወንጌል #ኑሮ #ስጡ #ቤተክርስቲያን #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #ገቢ

No comments:

Post a Comment