Popular Posts

Monday, July 31, 2017

የፍቅራችሁንም ድካም

በጸሎታችን ጊዜ ስለ እናንተ ስናሳስብ፥ የእምነታችሁን ስራ የፍቅራችሁንም ድካም በጌታችንም በኢየሱስ ክርስቶስ ያለውን የተስፋችሁን መጽናት በአምላካችንና በአባታችን ፊት ሳናቋርጥ እያሰብን፥ እግዚአብሔርን ሁል ጊዜ በሁላችሁ ምክንያት እናመሰግናለን፤ 1 ተሰሎንቄ 1፡2-3
ፍቅር ስሜት አይደለም፡፡ ፍቅር ከእኛ ቁጥጥር ውጭ የሆነ በፈለገው ጊዜ የሚይዘን በፈለገው ጊዜ ደግሞ የሚለቀን ምትሃት ወይም ስሜት አይደለም፡፡ እውነተኛ ፍቅር የውሳኔ ድርጊት ነው፡፡ እውነተኛ ፍቅር የመረዳት እርምጃ ነው፡፡ እውነተኛ ፍቅር የማስተዋል ስራ ነው፡፡
ፍቅር የሚታየው በስራ ነው፡፡ ፍቅር የሚታየው በድርጊት ነው፡፡ ፍቅር የሚገለፀው በድካም ነው፡፡
ሃዋሪያው ጳውሎስ እግዚአብሄርን የሚያመሰግነው የፍቅራቸውን ድካም አይቶ ነው፡፡ የተሰሎንቄ ሰዎች ፍቅራቸው የተገለፀው በስራቸው ነው፡፡ ፍቅራቸውን የገለጠው ትጋታቸው ነው፡፡ እንዲሰሩ እንዲደክሙ ያደረጋቸው ፍቅር ነው፡፡ እነዚህ የተሰሎንቄ ሰዎች ፍቅር ስላላቸው ለሚወዱት ይሰራሉ ፣ ለሚወዱት ይተጋሉ ብሎም ለሚወዱት ይደክማሉ፡፡
ለፍቅር እንድከም እንጂ ቢደክመን ችግር የለውም፡፡ በፍቅር ትጋት ይጠበቃል፡፡ በፍቅር ስራ ግዴታ ነው፡፡ እንዲያውም በልባችን ያለው ፍቅር ወጥቶ የሚታየው በድርጊትና በስራ ነው፡፡
በጸሎታችን ጊዜ ስለ እናንተ ስናሳስብ፥ የእምነታችሁን ስራ የፍቅራችሁንም ድካም በጌታችንም በኢየሱስ ክርስቶስ ያለውን የተስፋችሁን መጽናት በአምላካችንና በአባታችን ፊት ሳናቋርጥ እያሰብን፥ እግዚአብሔርን ሁል ጊዜ በሁላችሁ ምክንያት እናመሰግናለን፤ 1ኛ ተሰሎንቄ 1፡2-3
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #ፍቅር #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #ቸርነት #ትግስት #ፍርሃት #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #መውደድ #ትግስት #መሪ


No comments:

Post a Comment