ነገር ግን እላለሁ፥ በመንፈስ ተመላለሱ፥ የሥጋንም ምኞት ከቶ አትፈጽሙ። ገላትያ 5፡16
ክርስትያኖች በመንፈስ እንድንመላለስ ታዘናል፡፡
በክርስትያ ስኬታማ የምንሆነው በመንፈስ ስንመላለስ ብቻ ነው፡፡ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለመፈፀም በመንፈስ መመላለስ ሌላ አማራጭ
የሌለው ነገር ነው፡፡
1.
በመንፈስ መመላለስ የአትያዝ፥
አትቅመስ፥ አትንካ ጉዳይ አይደለም፡፡
በመንፈስ መመላለስ
ማለት አትያዝ፥ አትቅመስ፥ አትንካ በሚሉ ህጎች መኖር ማለት አይደለም፡፡ እነዙህ ንጎች ሰውን የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንዲፈፅም
የሚጠቅሙ ቢሆኑ በብሉይ ኪዳን የእግዚአብሔር ህዝብ እግዚአብሔርን ባስደሰተው ነበር፡፡ አትያዝ፥ አትቅመስ፥ አትንካ የሚሉ ህጎች
የእግዚአብሔርን አላማ እንድንፈፅም የሚረዱ ቢሆኑ ኖሮ ኢየሱስ ለሃጢያታችን መሞትና መንፈስ ቅዱስ መሰጠቱ አለዓስፈለገም ነበር፡፡
አትያዝ፥ አትቅመስ፥ አትንካ በሚሉት ህንጎች የእግዚአብሔርን መንገድ መጠበቅ የምንችል ቢሆን ኖሮ መንፈስ ቅዱስ በእኛ ውስጥ መኖርና
መምራት አያስፈልገውም ነበር፡፡
እንደ ሰው ሥርዓትና
ትምህርት። አትያዝ፥ አትቅመስ፥ አትንካ ለሚሉት ትእዛዛት በዓለም እንደምትኖሩ ስለ ምን ትገዛላችሁ? እነዚህ ሁሉ በመደረግ ሊጠፉ
ተወስነዋልና። ቆላስያስ 2፡22
2.
በመንፈስ መመላለስ በሆነ ደመና
ውስጥ መመላለስ ማለት አይደለም፡፡
በመንፈስ መመላለስ
ማለት የሆነ ልዩና የማይደረስበት መንፈሳዊ ልምምድ ውስጥ መግባት ማለት አይደለም፡፡ በመንፈስ መመላለስ ማንም ክርስትያን ሊያደርገው
የሚችለው ነገር ነው፡፡ በመንፈስ መመላለስ እያንደሳንዱ ክርስትያን እንዲያደርገው የታዘዘውም ነገር ነው፡፡ በመንፈስ መመላለስ ባንታዘዘው
ሃጢያት የሚሆንብን የእግዚአብሔር ሊፈፀም የሚችል ትእዛዝ ነው፡፡ በመንፈስ መመላለስ ጥቂት የተመረጡ ሰዎች እንደ እድል የሚገቡበት
ልምምድ ሳይሆን ጌታ ኢየሱስን እንደ አዳኝና ጌታ የተቀበልን ሁላችን በየእለቱና በየደቂቃው የምንኖረው የህይወት ዘይቤ ነው፡፡
ነገር ግን እላለሁ፥
በመንፈስ ተመላለሱ፥ የሥጋንም ምኞት ከቶ አትፈጽሙ። ገላትያ 5፡16
3.
በመንፈስ መመላለስ የእግዚአብሔር
መንፈስ በእኛ ውስጥ መኖሩ ማለት ነው፡፡
የእግዚአብሔ ህይወት
በእኛ ውስጥ ይኖራል፡፡ ይህ የእግዚአብሔር ህይወት ይመራናል፡፡ ይህ የእግዚአብሔር ህይወት ሃይልን ይሰጠናል፡፡ ይህ የእግዚአብሔር
ህይወት በውስጣችን መኖሩ በመንፈስ እንድንኖር ያደርገናል፡፡
እናንተ ግን የእግዚአብሔር መንፈስ በእናንተ ዘንድ ቢኖር፥ በመንፈስ እንጂ በሥጋ አይደላችሁም። የክርስቶስ መንፈስ የሌለው ከሆነ ግን ይኸው የእርሱ ወገን አይደለም። ሮሜ 8፡9
4.
በመንፈስ መመላለስ በእግዚአብሔር
ቃል ሃሳብ መኖር ማለት ነው፡፡
በመንፈስ መመላለስ ማለት የእግዚአብሔርን ቃል ማሰብ ማለት ነው፡፡ በመንፈስ መመላለስ ማለት እንደቃሉ መመላለስ ማለት ነው፡፡ በመንፈስ መመላለስ ማለት ከቃሉ ውጭ የሆነን ነገር አለማሰብ ማለት ነው፡፡ በመንፈስ መመላለስ ማለት እንደቃሉ ማሰብ መናገር እና ማድረግ ማለት ነው፡፡
በመንፈስ መመላለስ ማለት የእግዚአብሔርን ቃል ማሰብ ማለት ነው፡፡ በመንፈስ መመላለስ ማለት እንደቃሉ መመላለስ ማለት ነው፡፡ በመንፈስ መመላለስ ማለት ከቃሉ ውጭ የሆነን ነገር አለማሰብ ማለት ነው፡፡ በመንፈስ መመላለስ ማለት እንደቃሉ ማሰብ መናገር እና ማድረግ ማለት ነው፡፡
እንደ ሥጋ ፈቃድ የሚኖሩ የሥጋን ነገር ያስባሉና፥ እንደ መንፈስ ፈቃድ የሚኖሩ ግን የመንፈስን ነገር ያስባሉ። ስለ ሥጋ ማሰብ ሞት ነውና፥ ስለ መንፈስ ማሰብ ግን ሕይወትና ሰላም ነው። ስለ ሥጋ ማሰብ በእግዚአብሔር ዘንድ ጥል ነውና፤ ለእግዚአብሔር ሕግ አይገዛምና፥
መገዛትም ተስኖታል፤ ሮሜ 8፡5-7
5.
በመንፈስ መመላለስ የእግዚአብሔርን
ህግ ሁሉ መፈፀም ነው፡፡
በመንፈስ የሚመላለስ ሰው እያንዳንዱን የብሉይ ኪዳን ህጎች መጠበቅ
ሳያስፈልገው በመንፈስ በመመላለስ ብቻ በራሱ ሁሉንም የእግዚአብሔርን ህግ ይፈፅመዋል፡፡ መንፈስ ወደ እግዚአብሔር ፈቃድ ስለሚመራ
በመንፈስ የሚመላለስ ሰው በዝርዝር ሳያውቀው የእግዚአብሔርን ህግ ይፈፅመዋል፡፡ በመንፈስ የሚመላለስ ሰው በህጉን ሁሉ ፀሃፊ ስለሚመላለስ
የሚስተው አንድም የእግዚአብሔር ህግ የለም፡፡ በመንፈስ የሚመላለሰ ሰው የቱን ህግ እየፈፀምኩ ነው ብሎ በአእምሮው ሳይመራመር የእግዚአብሔርን ፈቃድ ሲፈፅም ራሱን ያገኘዋል፡፡
እንደ ሥጋ ፈቃድ ብትኖሩ ትሞቱ ዘንድ አላችሁና፤ በመንፈስ ግን የሰውነትን
ሥራ ብትገድሉ በሕይወት ትኖራላችሁ። ሮሜ 8፡13
ለተጨማሪ
ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ
መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ
#ጌታ #የመንፈስፍሬ
#በመንፈስመመላለሰ #ቃሉንማሰላሰል #መንፈስበእኛ #ህግንመፈፀም #ባህሪ
#ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ
#የእግዚአብሔርህይወት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #በጎነት
#የዋሃት #ራስንመግዛት
#ትግስት #መሪ
No comments:
Post a Comment