Popular Posts

Monday, July 17, 2017

ብዙ ሰዎችንም ወደ ጽድቅ የሚመልሱ

ጥበበኞቹም እንደ ሰማይ ፀዳል፥ ብዙ ሰዎችንም ወደ ጽድቅ የሚመልሱ እንደ ከዋክብት ለዘላለም ይደምቃሉ። ዳንኤል 12፡3
እኔም እላችኋለሁ፥ የዓመፃ ገንዘብ ሲያልቅ በዘላለም ቤቶች እንዲቀበሉአችሁ፥ በእርሱ ወዳጆችን ለራሳችሁ አድርጉ። ሉቃስ 16:9
አሁን በምድር እያለን ትልቅ ነገር የሚሆንብን ብዙ ነገሮች ወደጌታ ስንሄድ ግን ትልቅ ነገር አይሆኑብንም፡፡ አሁን በምድር ላይ የሚመስጡን ነገሮች ወደጌታ ስንሄድ ምን ያህል ከንቱ እንደሆኑ እንረዳለን፡፡ አሁን ክብደት የምንሰጣቸው ነገሮች ወደ ሰማይ ስንሄድ ያን ያክል ክብደት በመስጠት የሚገባንን ያህል የጌታን ወንጌል አለመመስከራችን ያሳዝነናነል፡፡  
የሚታየው ነገር ሁሉ ጊዜያዊ ነው፡፡ የማይታየው ግን ዘለዓለማዊ ነው፡፡ ወደጌታ ስንሄድ ጉዳዬ ልንለው የሚገባው አንድ ነገር ነው፡፡ በምድር ላይ የምን ያህል ሚሊየን ቤት ውስጥ መኖራችን ሰማይን አያስገርመውም፡፡ ባለን በማንኛውም ነገር ተጠቅመን ምን ያህል ሰዎችን ወደ መንግስተሰማያት እንዲገቡ መርዳታችን እንጂ በምድር ላይ ምን ያህል ዝነኛ መሆናችን ሰማይን አይገርመውም፡፡  
እንዲያውም እግዚአብሄር የሰጠንን እድል በህይወትም ሆነ በቃል ለብዙዎች ስለጌታ አዳኝነት በመመስከር ብዙዎችን ወደጌታ ማምጣት ባለብን ጊዜ ጊዜያዊ ለሆነው የምድር ኑሮ ብናባክነው እግዚአብሄር ደስ አይሰኝም፡፡
ለሌላው የምንመሰክርበትና ሌላው ጌታን እንዲያይ የምንረዳበትን ጊዜያችንን ፣ ጉልበታችን ፣ እውቀታችንንና ገንዘባችንን በሚያልፍ በምድርራዊ ሃብትና ዝና በማከማቸት በማባከናችን ህይወታቸንን እናባክናለን፡፡
እግዚአብሄር የሚያስፈልገንን ነገር ሁሉ የሚያሟላው እኛ በእግዚአብሄር የመንግስቱ የወንጌል ስራ ላይ እንድንጠመድና ለምድር ጨው የአለምም ብርሃን እንድንሆን ነው፡፡ በህክምና ፣ በትምህርት ፣ በኢንደስትሪ በእርሻ ዘርፍ ባለንበት የስራ መስካችን ሁሉ በህይወታችን ለብዙዎች ብርሃን ለመሆንና የመንግስተ ሰማያትን መንገድ ለማሳየት ነው፡፡
እነዚሀ በድርጊትና በቃል የጌታን አዳኝነት እንዲያዩ የረዳናቸው ሰዎች ሁሉ የዘላለም ሃብታችን ናቸው፡፡ በሰማይ እንግዲህ ጉዳዬ የምንለው በምድር የለበስነው ውድ ልብስ ወይም የነዳነው ዘመናዊ መኪና ሳይሆን በጊዜያዊ በምድራዊ ገንዘብ ተጠቅመን ስለጌታ ወንጌል የምንመሰክርላቸው ሰዎች ናቸው፡፡
እኔም እላችኋለሁ፥ የዓመፃ ገንዘብ ሲያልቅ በዘላለም ቤቶች እንዲቀበሉአችሁ፥ በእርሱ ወዳጆችን ለራሳችሁ አድርጉ። ሉቃስ 16:9
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#እምነት #ወንጌል #ስብከት #ቃል #ዝራ #የምድርጨው #የአለምብርሃን #የአመፃገንዘብ #የእግዚአብሄርሃይል #መንፈስቅዱስ #ቃሉንመስማት #እወጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ  

No comments:

Post a Comment