Popular Posts

Tuesday, July 25, 2017

የመንግስቱ ኢኮኖሚ - ኢንቨስትመንት

ኢንቨስትመንት ማለት በአንድ አትራፊ ነገር ላይ መዋእለ ኑዋይን ማፍሰስ ማለት ነው፡፡
በተለይ ገንዘባችንን ለእግዚአብሄር ቤት ሰጥተን ፣ መሰረታዊ ፍላጎታችንን አሟልተን የሚተርፈውን ገንዘብ መልሰን ኢንቨስት ብናደርገው ተጨማሪ ውጤት ይሰጠናል፡፡
ገንዘብን ጥሩ ወለድ በሚሰጥበት ባንክ በማስቀመጥ ጥሩ የወለድ ትርፍ ማግኘት ያቻላል፡፡
ስለዚህ ገንዘቤን ለለዋጮች አደራ ልትሰጠው በተገባህ ነበር፥ እኔም መጥቼ ያለኝን ከትርፉ ጋር እወስደው ነበር። ማቴዎስ 25፡27
እኛን በግል የማይፈልገን እንደ አክሲዮን በመግዛት ገቢያችንን ማሳደግ እንችላለን፡፡ እንዲሁም ንብረት በመግዛትና በማከራየት በመሳሰሉት ላይ ኢንቨስት ብናደርገው ስራው እኛን በግል ሳይፈልገንና ተቀጣሪ ሳያደርገን ገቢያችንን ያሳድጋል፡፡ እንዲሁም እኛን በግል የማይፈልግ ኢንቨስትመንት ስራ መስራት ባልቻልንበት ጊዜ እንኳን ገንዘባችን ለእኛ ስለሚሰራ ገቢያችን አይቋረጥም፡፡    
ኢንቨስትመንት ተቀጥረን ከምንሰራበት ከምናገኘው ገንዘብ በተጨማሪ እኛን በግል የማይፈልገን ኢንቨስትመንትና ትርፍ ይኖረናል ማለት ነው፡፡
ከዚህም በተጨማሪ የግል ስራችንን ብንሰራ እንኳን ከስራችን ጋር ተያያዥነት ያላቸው ስራዎች ላይ ኢንቨስት በማድረግ የገቢያችንን አይነትና መጠን ማብዛት እንችላለን፡፡
ለምሳሌ ጋራዥ ያለው ሰው ተጨማሪ ገንዘቡን የተበላሸ መኪና ገዝቶ በመጠገን መኪና በማሻሻጥ በመሳሰኩት ላይ ተጨማሪ ገንዘብ ኢንቨስት ቢያደርግ ተጨማሪ ትርፍ ያገኛል ለእግዚአብሄርም መንግስት የሚሰጠው ገንዘብ ይበዛል፡
የበጎችህን መልክ አስተውለህ እወቅ፥ በከብቶችህም ላይ ልብህን አኑር፤ ባለጠግነት ለዘላለም አይኖርምና፥ ዘውድም ለትውልድ ሁሉ አይጸናምና። ደረቅ ሣር በታጨደ ጊዜ፥ አዲስ ለምለም በታየ ጊዜ፥ ከተራራውም ቡቃያ በተሰበሰበ ጊዜ፥ በጎች ለልብስህ ፍየሎችም የእርሻ ዋጋ ይሆናሉ። ለሲሳይህ ለቤተ ሰቦችህም ሲሳይ ለገረዶችህም ምግብ የፍየል ወተት ይበቃል። ምሳሌ 2713
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ኢንቨስትመንት #ገቢ #ብልፅግና #የብልፅግናወንጌል #ስራ #ትጋት #በረከት #ስኬት #ስምረት #መሰረታዊፍላጎት #ጥበብ #ሁሉየእናንተነውና #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #የተትረፈረፈህይወት #መፅሃፍቅዱስ #መድከም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment