Popular Posts

Monday, July 24, 2017

የመንግስቱ ኢኮኖሚ - ገንዘብን ማስቀመጥ

በምድር ስንኖር በጥበብ መኖር እጅግ ወሳኝ ነገር ነው፡፡ ከገንዘብና ከሃብት በላይ እንዴት እንደምናስተዳደረው ማወቅ ገንዘቡን ለሚገባው አላማ እንድናውለው ይረዳል፡፡ ጥበብ ከብዙ ውጣ ውረዶች ይጠብቀናል፡፡
በወርቅና በብር ከመነገድ ይልቅ በእርስዋ መነገድ ይሻላልና። ምሳሌ 3፡14
ገንዘብን ማጠራቀም ወይም መጠባበቂያ ገንዘብን ማስቀመጥ በጣም ጠቃሚ በመሆኑ ካላስፈላጊ ውጣ ውረዶች ያድነናል፡፡ አንዳንድ ወር ወጭው ይበዛል፡፡ ሌላው ወር ደግሞ ወጭው ያንሳል፡፡ በዚህ መሰረታዊ ፍላጎታችንን ካሟላን በኋላ የግዴታ የቀረውን ገንዘብ ሁሉ በቅንጦት ላይ ማዋልና መጨረስ የለብንም፡፡ ከመሰረታዊ ፍላጎት ተረፍ ያለ ገንዘብ በሚመጣ ጊዜ ወደፊት ፍላጎት እንዳለ አውቀን የተረፈውን ገንዘብ አጥፍቶ አለመጨረስና መያዝ ያስፈልጋል፡፡
ያለንን ገንዘብ ሁሉ አጥፍቶ አለመጨረስ መፅሃፍ ቅዱሳዊ ጥበብ ነው፡፡
የከበረ መዝገብና ዘይት በጠቢብ ሰው ቤት ይኖራል፤ አእምሮ የሌለው ሰው ግን ይውጠዋል። ምሳሌ 21፡20
ገቢዎች ይለዋወጣሉ፡፡ ገቢ ሲለዋወጥ ኑሮዋችንም አብሮ ከፍና ዝቅ እንዳይል ገንዘብ ተረፍ ብሎ በሚለመጣበት ጊዜ ለወደፊት ማስቀመጥ ይጠቅማል፡፡    
በበጋ የሚያከማች ልጅ አስተዋይ ነው፤ በመከር የሚተኛ ግን እርሱ ራሱን ያስነውራል። ምሳሌ 10፡5
ከመሰረታዊ ፍላጎት የተረፈውን ስናስቀምጠው ነው በተሻለ ነገር ላይ ማፍሰስ የምንችለው፡፡ ስናጠራቅም ብቻ ነው ገቢያችንን ለማስፋት በተለያዩ ነገሮች ላይ ኢንቨስት የምናደርገው፡፡  
የበጎችህን መልክ አስተውለህ እወቅ፥ በከብቶችህም ላይ ልብህን አኑር፤ ባለጠግነት ለዘላለም አይኖርምና፥ ዘውድም ለትውልድ ሁሉ አይጸናምና። ደረቅ ሣር በታጨደ ጊዜ፥ አዲስ ለምለም በታየ ጊዜ፥ ከተራራውም ቡቃያ በተሰበሰበ ጊዜ፥ በጎች ለልብስህ ፍየሎችም የእርሻ ዋጋ ይሆናሉ። ለሲሳይህ ለቤተ ሰቦችህም ሲሳይ ለገረዶችህም ምግብ የፍየል ወተት ይበቃል። ምሳሌ 27፡13
ኢየሱስ በምድር አገልግሎቱ ገንዘብ የሚጠራቀምበት ኮሮጆ ነበረው፡፡
ይሁዳ ከረጢቱን የያዘ ስለ ሆነ፥ ኢየሱስ፦ ለበዓሉ የሚያስፈልገንን ግዛ፥ ወይም ለድሆች ምጽዋት እንዲሰጥ ያለው ለአንዳንዱ መስሎአቸው ነበርና። ዮሃንስ 13፡29
ይብዛም ይነስም እንጂ ሊቆጥብ ሊያጠራቅም ሊያስቀምጥ የማይችል ሰው የለም፡፡
የከበረ መዝገብና ዘይት በጠቢብ ሰው ቤት ይኖራል፤ አእምሮ የሌለው ሰው ግን ይውጠዋል። ምሳሌ 21፡20
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #ብልፅግና #የብልፅግናወንጌል #ስራ #ትጋት #በረከት #ስኬት #ስምረት #መሰረታዊፍላጎት #ጥበብ #ሁሉየእናንተነውና #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #የተትረፈረፈህይወት #መፅሃፍቅዱስ #መድከም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment