Popular Posts

Friday, July 21, 2017

የመንግስቱ ኢኮኖሚ - በስራ መትጋት

በህይወት ለመሳካት ጥበብ ያስፈልገናል፡፡
በወርቅና በብር ከመነገድ ይልቅ በእርስዋ መነገድ ይሻላልና። ምሳሌ 3:14
መፅሃፍ ቅዱስ ደግሞ ለሰው ልጅ ስኬት የሚያስፈልገውን ጥበብ ሁሉ ይዞዋል፡፡ መፅሃፍ ቅዱስ የማይዳስሰው ለሰው አስፈላጊ የሆነ የህይወት ክፍል የለም፡፡
መፅሃፍ ቅዱስ ስለገንዘብ አያያዛችን ያስተምራል፡፡ መፅሃፍ ቅዱስ ገንዘብን እንዴት እንደምናገኝ ፣ ገንዘብን እንዴት እንደምናጠራቅም ፣ ገንዘብን እንዴት እንደምንሰጥና ገንዘብን እንዴት እንደምንጠቀም በጥበብ የተሞላ ነው፡፡
ምንም እንኳን የመጀመሪያው ጥሪያችን የእግዚአብሄርን መንግስትና ፅድቁን መፈለግ ቢሆንም እግረ መንገዳችንን ገንዘብ እናገኛለን፡፡ የመጀመሪያው ሙያችን ክህነት ቢሆንም በተሰማራንበት የስራ መስክ በምድር ላይ የሚያስፈልገንን ወጭ ለመሸፈን ገንዘብን እናገኛለን፡፡ እግረመንገዳችንን በትጋታችን የእግዚአብሄርን መልካምነትና ፀጋ ምስክር እንሆናለን፡፡
ባሪያዎች ሆይ፥ በቅን ልብ ጌታን እየፈራችሁ እንጂ፥ ለሰው ደስ እንደምታሰኙ ለታይታ የምትገዙ ሳትሆኑ፥ በሥጋ ጌቶቻችሁ ለሆኑ በሁሉ ታዘዙ። ለሰው ሳይሆን ለጌታ እንደምታደርጉ፥ የምታደርጉትን ሁሉ በትጋት አድርጉት፥ ከጌታ የርስትን ብድራት እንድትቀበሉ ታውቃላችሁና፤ የምታገለግሉት ጌታ ክርስቶስ ነውና። ቆላስይስ 3፡22-24
ይህም ብቻ አይደለም አንደኛው በውጭ ካሉት ዘንድ ክብርን የምናገኘበት አንዱ መንገድ ስራን በመስራት የራሳችንን ወጭ ራሳችን በመሸፈን ነው፡፡
ነገር ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ከፊት ይልቅ ልትበዙ፥ በጸጥታም ትኖሩ ዘንድ ልትቀኑ፥ የራሳችሁንም ጉዳይ ልትጠነቀቁ፥ እንዳዘዝናችሁም፥ በውጭ ባሉት ዘንድ በአገባብ እንድትመላለሱ፥ አንዳችም እንዳያስፈልጋችሁ በእጃችሁ ልትሠሩ እንለምናችኋለን። 1ኛ ተሰሎንቄ 4፡10-12
የምናደርገውን ስራ ሁሉ በትጋት እንድናደርግ መፅሃፍ ቅዱስ ያዘናል፡፡
የታካች እጅ ችግረኛ ታደርጋለች፤ የትጉ እጅ ግን ባለጠጋ ታደርጋለች። ምሳሌ 104
የታካች ሰው ነፍስ ትመኛለች፤ አንዳችም አታገኝም፤ የትጉ ነፍስ ግን ትጠግባለች። ምሳሌ 13፡4
ለመስራትና መድከም በህይወት ያለ ሰው እድልና ጥቅም እንደሆነና ይህንን እድል በሙላት እንድንጠቀምበት መፅሃፍ ቅዱስ ያስተምራል፡፡
አንተ በምትሄድበት በሲኦል ሥራና አሳብ እውቀትና ጥበብ አይገኙምና እጅህ ለማድረግ የምታገኘውን ሁሉ እንደ ኃይልህ አድርግ። መክብብ 9፡10
ከራሳችን አልፈን ለሌሎች መልካም ማድረግ የምንችለው ፣ በእግዚአብሄር መንግስት ላይ ሃብታችንን ማፍሰስ የምንችለውና የክርስቶስን ቤተክርስቲያን መገደፍ የምንችለው በትጋት ስንሰራ ነው፡፡ ተግተን ለመስራት ሃብትን ለማከማቸት ተባርከን ለበረከት እንድንሆን ጉልበትን የሚሰጠን እግዚአብሄር ይባረክ፡፡
ነገር ግን ዛሬ እንደ ሆነ ለአባቶችህ የማለውን ቃል ኪዳን ያጸና ዘንድ፥ ሀብት ለማከማቸት እርሱ ጉልበት ሰጥቶሃልና አምላክህን እግዚአብሔርን አስብ። ዘዳግም 8፡18
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ብልፅግና #የብልፅግናወንጌል #ስራ #ትጋት #በረከት #ስኬት #ስምረት #መሰረታዊፍላጎት #ጥበብ #ሁሉየእናንተነውና #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #የተትረፈረፈህይወት #መፅሃፍቅዱስ #መድከም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment