Popular Posts

Wednesday, July 19, 2017

ወንጌልን ለማካፈል የሚጠቅሙ ነጥቦች

ወንጌልን ለማካፈል የተወሰነ ቀመር የለውም፡፡ ሰው እግዚአብሄር ያደረገለትን በራሱ ቋንቋና መንገድ ሊመሰክር ይችላል፡፡ በአጠቃላይ ግን ወንጌልን ለሌሎች ለመመስከር የሚጠቅሙ አምስት ነጥቦችን ከመፅሃፍ ቅዱስ እንመልከት፡-
1.      እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረው ፍፁም አድርጎ በመልኩና በአምሳሉ ነበር ፡፡
እግዚአብሔርም አለ፦ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፤ የባሕር ዓሦችንና የሰማይ ወፎችን፥ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ። እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው። ዘፍጥረት 1፡26-27
2.     ሰው እግዚአብሄር አታድርግ ያለውን በማድረጉ ምክኒያት በአመፃው ከእግዚአብሔር ተለያየ፡፡
ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤ ሮሜ 3፡23
3.     የሰውም መጥፋት የማይፈልግ እግዚአብሄር አለምን ካለምክኒያት እንዲሁ ስለወደደ ሃጢያት የማያውቀውን እንድ ልጁን ኢየሱስን ስለሃጢያታችን በመስቀል ላይ እንዲሞት ፈቀደ፡፡
ኃጢአተኞችን ሊያድን ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዓለም መጣ የሚለው ቃል የታመነና ሁሉ እንዲቀበሉት የተገባ ነው፤ ከኃጢአተኞችም ዋና እኔ ነኝ፤ 1ኛ ጢሞቴዎስ 1፡15
በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና። ዮሃንስ 3፡16
4.     ኢየሱስ በመስቀል ላይ የሃጢያት ዋጋችንን ሁሉ ከፍሎዋል፡፡
እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንሆን ዘንድ ኃጢአት ያላወቀውን እርሱን ስለ እኛ ኃጢአት አደረገው። 2ኛ ቆሮንቶስ 5፡21
ስለ በደላችን አልፎ የተሰጠውን እኛን ስለ ማጽደቅም የተነሣውን ጌታችንን ኢየሱስን ከሙታን ባስነሣው ለምናምን ለእኛ ይቈጠርልን ዘንድ አለው። ሮሜ 4፡24-25
5.     ኢየሱስ ስለሃጢያትችን እንደሞተና የሃጢያት እዳችንን እንደከፈለ ሞትን ድል አድርጎ እንደተነሳ ብናምንና ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ በአፋችን ብንመሰክር እንድናለን ፣¸እግዚአብሄር ልጅ አድርጎ ይቀበለናል ፣ የዘላለም ህይወት ይሰጠናል እንዲሁም ኢየሱስ በልባችን በመኖር በህይወት አሸናፊዎች ያደርገናል፡፡
ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤ ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናልና። ሮሜ 10፡9-10
ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤ ዮሃንስ 1፡12
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#እምነት #ወንጌል #ስብከት #ቃል #ዝራ #የምድርጨው #የአለምብርሃን #የአመፃገንዘብ #የእግዚአብሄርሃይል #መንፈስቅዱስ #ቃሉንመስማት #እወጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ  

No comments:

Post a Comment