Popular Posts

Wednesday, July 26, 2017

የአዲስ ኪዳን ነቢያት !

በብሉይ ኪዳን የእግዚአብሔር መንፈስ የሚያርፈው በጥቂት ሰዎች ላይ ነበር፡፡ በብሉይ ኪዳን በእግዚአብሔር መንፈስ የሚቀቡት ነቢያት ፣ ነገስታትና በካህናት ብቻ ነበሩ፡፡ ሌላው የእግዚአብሔር ህዝብ ከእግዚአብሔር መጠየቅ ቢፈልግ ወደ እነዚህ ወደ ነቢያት ፣ ወደ ካህናትና ወደነገስታት ነበር የሚሔደው፡፡ ስለዚህ ነው የብሉይ ኪዳን ሰዎች ስለህይወት ጥያቄያቸው እግዚአብሔርን መጠየቅ ሲፈልጉ ነቢያትን የሚፈልጉት፡፡
. . . ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤ እርሱም ዓለም የማያየውና የማያውቀው ስለ ሆነ ሊቀበለው የማይቻለው የእውነት መንፈስ ነው፤ ነገር ግን ከእናንተ ዘንድ ስለሚኖር በውሥጣችሁም ስለሚሆን እናንተ ታውቃላችሁ። ዮሃንስ 14፡15-17
ኢየሱስ በመስቀል ላይ የሃጢያት እዳችንን ከከፈከና ወደሰማይ ካረገ በኋላ መንፈስ ቅዱስ ወርዷል፡፡ ኢየሱስን እንደ አዳኝ እና ጌታ የተቀበሉት ሁሉ የእግዚአብሔርን መንፈስ ይቀበላሉ፡፡
ጴጥሮስም፦ ንስሐ ግቡ፥ ኃጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ። የተስፋው ቃል ለእናንተና ለልጆቻችሁ ጌታ አምላካችንም ወደ እርሱ ለሚጠራቸው በሩቅ ላሉ ሁሉ ነውና አላቸው። ሐዋርያት 2፡38-39
አሁን በአዲስ ኪዳን መንፈስ ቅዱስ ኢየሱስን በተቀበሉ ሰዎች ሁሉ ውስጥ ይኖራል፡፡ መንፈስ ቅዱስ ኢየሱስን በተቀበሉ ሰዎች ሁሉ ውስጥ ስለሚኖር በአዲስ ኪዳን ሰዎች እግዚአብሔርን መጠየቅ ሲፈልጉ ሲፀልዩና መንፈስ ቅዱስን ሲሰሙ እንጂ ወደ ነቢያት ሲሔዱና እግዚአብሔር ስለእኔ ምን አለህ ብለው ነቢያትን ሲጠይቁ አንመለከትም፡፡ አሁን የእግዚአብሔር መንፈስ በሁላችን ውስጥ ይኖራል፡፡
የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ አታውቁምን? 1ኛ ቆሮንቶስ 3፡16
በአዲስ ኪዳን ሁላችንም ተቀብተናል፡፡ በአዲስ ኪዳን ጌታን በተቀበልን በሁላችን ውስጥ የእግዚአብሔር ቅባት ይኖራል፡፡
እናንተም ከቅዱሱ ቅባት ተቀብላችኋል፥ ሁሉንም ታውቃላችሁ። እናንተስ ከእርሱ የተቀበላችሁት ቅባት በእናንተ ይኖራል፥ ማንም ሊያስተምራችሁ አያስፈልጋችሁም፤ ነገር ግን የእርሱ ቅባት ስለ ሁሉ እንደሚያስተምራችሁ፥ እውነተኛም እንደ ሆነ ውሸትም እንዳልሆነ፥ እናንተንም እንዳስተማራችሁ፥ በእርሱ ኑሩ። 1ኛ ዮሐንስ 2፡20፣27
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #የመንፈስፍሬ #ቅባት #መንፈስቅዱስ #የእግዚአብሔርመንፈስ #መሪ #ቤተመቅደስ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #የእግዚአብሔርህይወት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment