እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን
ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ። መዝሙር 33፡12
ነገር ግን አምላኩ የመሆን ትርጉም ምንድነው፡፡
ወይም እግዚአብሄር ለህዝብ አምላኩ ሆነ ማለት ምን ማለት ነው፡፡
እንዲሁም እናንተ ሕዝብ ትሆኑኛላችሁ እኔም አምላክ እሆናችኋለሁ። ኤርሚያስ
11፡4
እግዚአብሄር አምላኩ የሆነለት ማለት ፡-
1.
በእግዚአብሄር ፍቅር ካለምክኒያት
ተወደናል ማለት ነው፡፡
ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች
ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል። ሮሜ 5፡8
2.
እግዚአብሄር ስለእኛ ሃላፊነት
ይወስዳል ይመራናል ማለት ነው፡፡
ጌታን ለመከተል በወሰንን
በዚያን ጊዜ እግዚአብሄር በእኛ አምኖዋል፡፡ ልጆቼ ናቸው ብሎዋል፡፡ ስለእነርሱ ሃላፊነት እወስዳለሁ፡፡ ስለእነሱ እጠየቃለሁ ብሎዋል፡፡
ፍቅር . . . ሁሉን
ያምናል፥ 1ኛ ቆሮንቶስ 13፡7
3.
እግዚአብሄር ስለእኛ ተጠሪ
ነው ማለት ነው፡፡
ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤ ዮሃንስ 1፡12
ስለዚህም ምክንያት፦ ስምህን ለወንድሞቼ እነግራቸዋለሁ በማኅበርም መካከል በዜማ አመሰግንሃለሁ፤ ደግሞም፦ እኔ በእርሱ እታመናለሁ፤ ደግሞም፦ እነሆኝ እኔን እግዚአብሔር የሰጠኝንም ልጆች ሲል ወንድሞች ብሎ ሊጠራቸው አያፍርም። ዕብራውያን 2፡13
መልካም እረኛ እኔ ነኝ። መልካም እረኛ ነፍሱን ስለ በጎቹ ያኖራል። ዮሃንስ 10፡11
4.
እግዚአብሄር ስለእኛ ያቅዳል
በእቅዱም ይመራናል ማለት ነው፡፡
ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም።ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም። ኤርምያስ 29፡11
5.
እኛ የእግዚአብሄር
ነን ማለት ነው፡፡
በዋጋ ተገዝታችኋልና
ለራሳችሁ አይደላችሁም፤ 1ኛ ቆሮንቶስ 6፡19-20
እኔ በምሠራበት
ቀን እነርሱ የእኔ ገንዘብ ይሆናሉ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤
ሰውም የሚያገለግለውን ልጁን እንደሚምር፥ እንዲሁ እምራቸዋለሁ። ሚልክያስ 3፡17
በስሜ የተጠራውን ለክብሬም
የፈጠርሁትን፥ የሠራሁትንና ያደረግሁትን ሁሉ አምጣ እለዋለሁ። ኢሳይያስ 43፡7
6.
ከእግዚአብሄር እጅ ሊነጥቀን
የሚችል የለም ማለት ነው፡፡
እኔም የዘላለም ሕይወትን እሰጣቸዋለሁ፥ ለዘላለምም አይጠፉም፥ ከእጄም ማንም አይነጥቃቸውም። የሰጠኝ አባቴ ከሁሉ ይበልጣል፥ ከአባቴም እጅ ሊነጥቃቸው ማንም አይችልም። ዮሃንስ 10፡28-29
7.
እግዚአብሄር በእኛ ፋንታ ሃይሉን
ይገልጣል ማለት ነው፡፡
እግዚአብሔር ልቡ በእርሱ ዘንድ ፍጹም የሆነውን ያጸና ዘንድ ዓይኖቹ በምድር ሁሉ ይመለከታሉና።
አሁንም ስንፍና አድርገሃል፥ ስለዚህም ከዛሬ ጀምሮ ሰልፍ ይሆንብሃል። 2ኛ ዜና 16፡9
8.
እግዚአብሄር ከፊታችን ይወጣል
ማለት ነው፡፡
እርሱም፦ አንተ ከእኛ ጋር ካልወጣህስ፥ ከዚህ አታውጣን። በምድርም ፊት ካለው ሕዝብ ሁሉ እኔና ሕዝብህ የተለየን እንሆን ዘንድ አንተ ከእኛ ጋር ካልወጣህ፥ እኔና ሕዝብህ በአንተ ዘንድ ሞገስ ማግኘታችን በምን ይታወቃል? አለው። ዘጸአት 33፡15-16
9.
ለክብሩ የፈጠረን ለክብሩ የሚጠቀምብን
ነን ማለት ነው፡፡
እግዚአብሔር እርሱ አምላክ እንደ ሆነ እወቁ፤ እርሱ ሠራን እኛም አይደለንም፤ እኛስ ሕዝቡ የማሰማርያውም በጎች ነን። መዝሙር 100፡3
10.
የእግዚአብሄር የሆነውን ተካፍለናል ማለት ነው፡፡
የመለኮቱ ኃይል፥ በገዛ ክብሩና በበጎነቱ የጠራንን በማወቅ፥ ለሕይወትና እግዚአብሔርን ለመምሰል የሚሆነውን ነገር ሁሉ
ስለ ሰጠን፥ በእግዚአብሔርና በጌታችን በኢየሱስ እውቀት ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ። 2ኛ የጴጥሮስ 1፡2-3
ሁሉ የእናንተ ነው፥ እናንተም የክርስቶስ ናችሁ ክርስቶስም የእግዚአብሔር ነው። 1ኛ ቆሮንቶስ 3፡23
#እግዚአብሔር #አምላክ
#የተባረከ #የተመሰገነ #የታደለ #የተሞገሰ #የተወደደ #የተከናወነ #የተሳካ #የተለየ #የከበረ #የሚቀናበት #የተጠቀመ #እድለኛ
#ክብር #ምሪት #ሰላም #ቃል #እረፍት #አምልኮ #ኢየሱስ #ጌታ #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ
#አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment