በችኰላ የምትከማች ሀብት ትጐድላለች፤ ጥቂት በጥቂት የተከማቸች ግን ትበዛለች። ምሳሌ
13፡11
በመጀመሪያ ፈጥኖ የተከማቸ ርስት ፍጻሜው አይባረክም። ምሳሌ 20፡21
የታመነ ሰው እጅግ ይባረካል፤ ባለጠጋ ለመሆን የሚቸኵል ግን ሳይቀጣ አይቀርም። ምሳሌ 28፡20
በስርቆት
የተከማቸች ሃብት የፅድቅ መሰረት ስለሌላት ትፈርሳለች፡፡
በስራና
በድካም የተከማቸች ሃብት ሰፊ መሰረት ስላላት ትበዛለች፡፡
በማጭበርበርና
በውሸት የተሰበሰበች ሃብት የተሳሳተ ዘር ስለሆነች መብዛት ያቅታታል፡፡
በንፅህናና
በመጠበቅ የተገኘች ሃብት መልካም ዘር ስለሆነች ትበዛለች፡፡
በጭቆና
የተከማቸች ሃብት ፍፃሜዋ አያምርም፡፡
በንፅህና
የተከማቸች ሃብት ፍፃሜዋ አስተማማኝ ነው፡፡
በአቋራጭ
የተገኘ ሃብት በንፅህና አይገኝም፡፡
በእግዚአብሄር
መንገድ ያልተገኘ ሃብት ባለሃብቱ ንፁህ ሊሆን አይችልም፡፡
ጥቂት
በጥቂት የተከማቸ ሃብት ይበዛል፡፡
በአቋራጭ
የተገኘ ሃብት የሚገኘው ገንዘብን በመውደደ ሰውንና እግዚአብሄርን ባለመውደድ ነው፡፡
የእግዚአብሄርን
መንገድ ጠብቆ በጊዜ መካከል የተገኘ ሃብት ምንም ሊሆን አይችልም አስተማማኝነቱ የተረጋገጠ ነው፡፡
በእግዚአብሄር
መንገድ ያልሆነ ገንዘብ በሙስና ፣ በስርቆትና በማጭበርበር ይመጣል፡፡
በታማኝነት
ከእኛ ጋር አብሮ ያደገ ሃብት ከእግዚአብሄር ነው፡፡
ለተጨማሪ
ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ
መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ
#ጌታ #ብልፅግና #የብልፅግናወንጌል #ችኮላ #ሃብት
#በረከት #ጥቂትበጥቂት #እረኛእግዚአብሄር #ስምረት #መሰረታዊፍላጎት #የታመነ
#ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #የተትረፈረፈህይወት #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #መርካት #ደስታ #የልብስፋት #ማስተዳደር #እረፍት
No comments:
Post a Comment