Popular Posts

Thursday, July 20, 2017

እምነት ጨምርልን

ሐዋርያትም ጌታን፦ እምነት ጨምርልን አሉት። ጌታም አለ፦ የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያህል እምነት ቢኖራችሁ፥ ይህን ሾላ፦ ተነቅለህ ወደ ባሕር ተተከል ብትሉት፥ ይታዘዝላችሁ ነበር። ሉቃስ 17፡5-6
ለስጋችንና ለምስኪን እኔ አስተሳሰባችንን የሚመቹ ነገር ግን መፅሃፍ ቅዱሳዊ ያልሆኑ የፀሎት ርእሶች አሉ፡፡ ከእነዚህ መካከል እምነትን ጨምርልን የሚለው አንዱ ነው፡፡
ሃዋሪያት ኢየሱስን እምነትን ጨርልን ሲሉት "እሺ ተቀበሉ እምነትን እየጨመርኩላችሁ ነው" አላላቸውም፡፡ ኢየሱስ ያለው ያላችሁን ትንሽ የምትመስለውን እምነት ተጠቀሙ ስራ ስሩባት ለውጥን ታመጣለች ነው፡፡ ኢየሱስ የሚለው ነገራችሁን ለመለወጥ የሚያስፈልጋችሁ ያላችሁ ትንሽ የምትመስለው እምነት ብቻ ነች፡፡ ኢየሱስ የሚለው የሰናፍጭ ቅንጣት ያህል የሆነችውን እምነት መጠቀም አለባችሁ ለውጥ የሚመጣው በእርሱ ነው፡፡
የእምነት ትንሽ የለውም፡፡ እምነት ሁሉ ይሰራል፡፡ ያላችሁን እምነት ብትጠቀሙ ለውጥ ይመጣል፡፡ እምነት ጥቅም ላይ ሲውል ሁልጊዜ ታላቅን ስራን ይሰራል፡፡ የእምነት እርምጃን በመውሰድ ለውጥን ታያላችሁ፡፡
አንዳንድ ሰው የሚረካው በመለመን ብቻ ነው ፡፡ ባለው እምነት መጠቀም ፣ እርምጃ መውሰድ ፣ ስራ መስራትና ፍሬ ማፍራት አያውቅም፡፡ ስለዚህ በህይወቱ ለውጥን አያይም፡፡ ሰው የሚያስፈልገው አሁን ባለው እምነት መጠቀም ነው፡፡
ሐዋርያትም ጌታን፦ እምነት ጨምርልን አሉት። ጌታም አለ፦ የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያህል እምነት ቢኖራችሁ፥ ይህን ሾላ፦ ተነቅለህ ወደ ባሕር ተተከል ብትሉት፥ ይታዘዝላችሁ ነበር። ሉቃስ 17፡5-6
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #መናገር #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ቃል #ማሰላሰል #ማድረግ #ሁሉይቻላል #ጥርጥር #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment