Popular Posts

Monday, July 3, 2017

አራቱ የማይመለሱ የፀሎት አይነቶች

እግዚአብሄር የመርህ አምላክ ነው፡፡ እግዚአብሄር ጋር የሚደርስ ሰው ማድረግ የሚገባቸው ነገሮች አሉ፡፡ ወደ እግዚአብሄር የሚደርስ ማድረግ የማይገባቸው ነገሮች አሉ፡፡
ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና። ዕብራውያን 11፡6
ሰው በእግዚአብሄር መንገድ ካልፀለየ አይመለስለትም፡፡
1.      ከፈቃዱ የሚቃረን ፀሎት  
ከሰው አፍ የወጣውን ሁሉ እግዚአብሄር አይመልስም፡፡ በተለይ ከፈቃዱ የሚፃረንን ፀሎት እግዚአብሄር በፍፁም አይመልስም፡፡ ከባህሪው ጋር የሚቃረንን ልመና እግዚአብሄር አይመልስም፡፡
እንደ ፈቃዱ አንዳች ብንለምን ይሰማናል። 1ኛ ዮሐንስ 5፡14
2.     በቅንጦት የተፀለየ ፀሎት
ስንፀልይ የሚያስፈልገንን ነገር እንድንፀልይ መፅሃፍ ቅዱስ ያስተምረናል፡፡ የእኛን የምኞት ጥያቄ እንደሚመለስ በየትኛውም የመፅሃፍ ቅዱስ ክፍል ቃል አልተገባልንም፡፡ ስለዚህ ከመፀለያችን በፊት እውነተኛ ፍላጎት መሆኑን ማረጋገጥ አለብን፡፡ ስለዚህ ነው ለመፀለይ መቸኮል የሌለብን ፡፡ ለመፀለይ ምን እንደሚያስፈልገን ለማወቅ ጊዜ መሰጠት ያለብን፡፡ እንድ ጊዜ ፍላጎታችንን ካወቅን የሚመለስ ፀሎትን ለመፀለይ ቀላል ይሆንልናል፡፡
ስለዚህ ነው መንፈስ ቅዱስ እንዴት እንደምንፀልይ ያለማወቅ ድካማችንን የሚያግዘን፡፡ ሮሜ 8፡26
ትለምናላችሁ፥ በምቾቶቻችሁም ትከፍሉ ዘንድ በክፉ ትለምናላችሁና አትቀበሉም። ያዕቆብ 4፡3
3.     በጥርጥር የተፀለየ ፀሎት
እግዚአብሄር እምነትን ከእኛ ይጠብቃል፡፡ እርሱ ለእኛ ያለውን ፍቅርና እንክብካቤ በመረዳት እንድንፀልይ ይፈልጋል፡፡ ልባችንን ከጥርጥር እንድናነፃ እግዚአብሄር ይፈልጋል፡፡
እውነት እላችኋለሁ፥ ማንም ያለው ነገር እንዲደረግለት ቢያምን በልቡ ሳይጠራጠር፥ ይህን ተራራ፦ ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር ቢል ይሆንለታል። ማርቆስ 11፡23
ነገር ግን በምንም ሳይጠራጠር በእምነት ይለምን፤ የሚጠራጠር ሰው በነፋስ የተገፋና የተነቃነቀ የባሕርን ማዕበል ይመስላልና። ሁለት አሳብ ላለው በመንገዱም ሁሉ ለሚወላውል ለዚያ ሰው ከጌታ ዘንድ አንዳች እንዲያገኝ አይምሰለው። ያዕቆብ 1፡6-8
4.     በማጉረምረም የሆነ ፀሎት
ወደእግዚአብሄር የመቅረብ ፕሮቶኮሉ ምስጋና ነውለእግዚአብሄርነቱና ለመልካምነቱ እውቅና መስጠት ግድ ይላል፡፡ ነገር ግን እግዚአብሄር ምንም አድርጎልን እንደማያውቅ እግዚአብሄርን ለመውቀስ የምንወረውርው ቃል እግዚአብሄር አይመልሰውም፡፡
እግዚአብሔር እርሱ አምላክ እንደ ሆነ እወቁ፤ እርሱ ሠራን እኛም አይደለንም፤ እኛስ ሕዝቡ የማሰማርያውም በጎች ነን። ወደ ደጆቹ በመገዛት፥ ወደ አደባባዮቹም በምስጋና ግቡ፤ አመስግኑት፥ ስሙንም ባርኩ፤ መዝሙር 100፡3-4
ከእነርሱም አንዳንዶቹ እንዳንጎራጎሩ በሚያጠፋውም እንደ ጠፉ አታንጐርጕሩ። 1ኛ ቆሮንቶስ 10፡10
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #የእግዚአብሄርፈቃድ #ፀሎት #ልመና #ማጉረምረም #ምስጋና #ቅንጦት #ጥርጥር #እንደፈቃዱ #መንፈስቅዱስ #እንዲሰማን #ቤተክርስትያን #አማርኛ #የእግዚአብሄርቃል #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #መጠየቅ #መንበርከክ #ይቃትታል

No comments:

Post a Comment