Popular Posts

Saturday, July 15, 2017

በማለዳ ዘርህን ዝራ፥ በማታም እጅህን አትተው

ደመናት ዝናብ በሞሉ ጊዜ በምድር ላይ ያፈስሱታል፤ ዛፍም ወደ ደቡብ ወይም ወደ ሰሜን ቢወድቅ፥ ዛፉ በወደቀበት ስፍራ በዚያ ይኖራል። ነፋስን የሚጠባበቅ አይዘራም፥ ደመናንም የሚመለከት አያጭድም። የነፋስ መንገድ እንዴት እንደ ሆነች አጥንትም በእርጉዝ ሆድ እንዴት እንድትዋደድ እንደማታውቅ፥ እንዲሁም ሁሉን የሚሠራውን የእግዚአብሔርን ሥራ አታውቅም። ወይም ይህ ወይም ማናቸው እንዲበቅል ወይም ሁለቱ መልካም እንዲሆኑ አታውቅምና በማለዳ ዘርህን ዝራ፥ በማታም እጅህን አትተው። መክብብ 11፡3-6
እግዚአብሄር ሰውን እንዴት እንደሚነካ አናውቅም
እግዚአብሄር ከእኛ የሚጠብቀው ሰውን ለመውቀስ የሚያስፈልገውን ቃል እንድንናገር ነው፡፡ ሰው የእግዚአብሄርን ቃል ካልሰማ አያውቅም ካላወቀ አይወቀስም፡፡ ከእግዚአብሄር ጋር አንብረን የምንሰራው ቃሉን በመናገር ነው፡፡ የምስራቹን ወንጌል የመናገር ሃላፊነት የእኛ ብቻ ነው፡፡  
የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናልና። እንግዲህ ያላመኑበትን እንዴት አድርገው ይጠሩታል? ባልሰሙትስ እንዴት ያምናሉ? ያለ ሰባኪስ እንዴት ይሰማሉ? ሮሜ 10፡13-14
አብዛኞቻችን ጌታን ለመቀበል በአንድ ቀን አልወሰንንም፡፡ ወንጌልን የነገሩን ሰዎች በእኛ ተስፋ አልቆረጡም ፡፡ ባገኙት አጋጣሚ ስለጌታ አዳኝነት ነገሩን፡፡ በነገሩን ቁጥር ስልገዘገዝ ስንገዘገዝ አንድ ቀን ወሰንን፡፡ ሰው እንዴትና መቼ እንደሚወስን አናውቅም፡፡ ብቸኛው ሃላፊነታችን አምኖ ሊወስንበት የሚያስችለውን ቃል መናገር ብቻ ነው፡፡  
የነፋስ መንገድ እንዴት እንደ ሆነች አጥንትም በእርጉዝ ሆድ እንዴት እንድትዋደድ እንደማታውቅ፥ እንዲሁም ሁሉን የሚሠራውን የእግዚአብሔርን ሥራ አታውቅም። መክብብ 11፡4-5
የእኛ ሃላፊነት በቀንም በማታም ቃሉን መዝራት ነው
ሰውን የማዳን ሃላፊነት የለብንም፡፡ የቱ እንደሚበቅል መቼ አንደሚበቅል አንዴት እንደሚበቅል አናውቅም፡፡ ያለብን ብቸኛው ሃላፊነት የወንጌልን ቃል መናገር ነው፡፡ ያለብን ሃላፊነት ወንጌልን ከመናገር አለመከልከል ነው፡፡ እግዚአብሄርን የሚጠይቀን ወንጌልን መናገራችንን እንጂ ማዳናችንን አይደለም፡፡
ነፋስን የሚጠባበቅ አይዘራም፥ ደመናንም የሚመለከት አያጭድም። መክብብ 11፡4
ወይም ይህ ወይም ያ ማናቸው እንዲበቅል ወይም ሁለቱ መልካም እንዲሆኑ አታውቅምና በማለዳ ዘርህን ዝራ፥ በማታም እጅህን አትተው። መክብብ 11፡6
ከእግዚአብሔርም ዘንድ ረድኤት ተቀብዬ ለታናሹም ለታላቁም ስመሰክር እስከዚች ቀን ድረስ ቆሜአለሁ፤ ሐዋርያት 26፡22-23
ደመናት ዝናብ በሞሉ ጊዜ በምድር ላይ ያፈስሱታል፤ ዛፍም ወደ ደቡብ ወይም ወደ ሰሜን ቢወድቅ፥ ዛፉ በወደቀበት ስፍራ በዚያ ይኖራል። ነፋስን የሚጠባበቅ አይዘራም፥ ደመናንም የሚመለከት አያጭድም። የነፋስ መንገድ እንዴት እንደ ሆነች አጥንትም በእርጉዝ ሆድ እንዴት እንድትዋደድ እንደማታውቅ፥ እንዲሁም ሁሉን የሚሠራውን የእግዚአብሔርን ሥራ አታውቅም። ወይም ይህ ወይም ያ ማናቸው እንዲበቅል ወይም ሁለቱ መልካም እንዲሆኑ አታውቅምና በማለዳ ዘርህን ዝራ፥ በማታም እጅህን አትተው። መክብብ 11፡3-6
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#እምነት #ወንጌል #ስብከት #ቃል #ዝራ #የእግዚአብሄርሃይል #መንፈስቅዱስ #ቃሉንመስማት #እወጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ  

No comments:

Post a Comment