Popular Posts

Friday, September 1, 2023

በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል ክፍል 3

 

እውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል . . . እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን። ትንቢተ ኢሳይያስ 534-5

እግዚአብሔር ሰውን ሲፈጥረው ጠንካራ እና ብርቱ አድርጎ ነው፡፡ ሰው ሲፈጠር በሽታ እና ደዌ አልነበረም፡፡ እግዚአብሔር የፈጠረው ሁሉ ለሰው መልካምነት የሚሰራ ነበር፡፡ የተለያዩ ድካሞች በሰው ላይ ስልጣን ያገኙት ሰው በእግዚአብሔር ላይ ካመፀ በሃላ ነበር፡፡

ሰው እግዚአብሔርን በሚታዘዝበት ጊዜ ሁሉ ምድር እና በምድር ያሉ ነገሮች ሁሉ ይታዘዙለት እና ይገዙለት ነበር፡፡ ሰው በሃጢያት ከመውደቁ በፊት በሰው ላይ የሚያምፅ አንድም ነገር አልነበረም፡፡

ሰው በእግዚአብሔር ላይ ሲያምፅ ነገሮች ሁሉ በሰው ላይ አመፁ፡፡ ሰው እግዚአብሔርን መታዘዝ ሲያቆም ነገሮች ሁሉ መታዘዛቸውን አቆሙ፡፡ ሰው ነገሮች ሁሉ የተነሱበት በእግዚአብሔር ላይ ከተነሳ በኋላ ብቻ ነው፡፡

ምድር ከአንተ የተነሣ የተረገመች ትሁን፤ በሕይወት ዘመንህም ሁሉ በድካም ከእርስዋ ትበላለህ፤ እሾህንና አሜከላን ታበቅልብሃለች፤ ኦሪት ዘፍጥረት 3፡17-18

ምድርንም ባረስህ ጊዜ እንግዲህ ኃይልዋን አትሰጥህም፤ ኦሪት ዘፍጥረት 4፡12

አሁንም እግዚአብሔር በክርስቶስ በኩል ከሃጢያት ሲበዠን ከበሽታም ተቤዠቶናል፡፡ ክርስቶስ ለነፍሳችን ሃጢያት ዋጋ ከፍ ለስጋችን ፈውስ ዋጋ ባይከፍል ኖሮ በምድር ላይ የእግዚአብሔርን አላማ በጥንካሬ እና በብርታት መፈፀም አንችልም ነበር፡፡

ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር፥ እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ፤ በመገረፉ ቁስል ተፈወሳችሁ። 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 2፡24

የነፍሳችን መዳን የመቤዠታችን ክፍል እንደሆነ ሁሉ የስጋ ፈውስ የመቤዠታችን አንዱ አካል ነው፡፡

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

#ኢየሱስ #ጌታ #ህማም #ደዌ #ወንጌል #ፈውስ #ጤንነት #ቤተክርስቲያን #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #መስቀል #በመገረፉ #ቁስል #ተፈወሳችሁ


No comments:

Post a Comment