በታካች
ሰው እርሻ፥ አእምሮ በጐደለውም ሰው ወይን ቦታ አለፍሁ። እነሆም፥ ሁሉ እሾህ ሞልቶበታል፥ ፊቱንም ሳማ ሸፍኖታል፥ የድንጋዩም ቅጥር ፈርሶአል። ተመለከትሁና አሰብሁ፤ አየሁትና ተግሣጽን ተቀበልሁ። ጥቂት ትተኛለህ፥ ጥቂትም ታንቀላፋለህ፥ ትተኛም ዘንድ ጥቂት እጅህን ታጥፋለህ፤ እንግዲህ ድህነትህ እንደ ወንበዴ፥ ችጋርህም ሰይፍ እንደ ታጠቀ ሰው ይመጣብሃል። ምሳሌ 24፡30-33
በአለም ላይ ለሁላችንም የሚበቃ ሃብት አለ፡፡
በአለም ውስጥ እጅግ ብዙ የተጠራቀመ ሃብት አለ፡፡ በአለም ውስጥ ብዙ ሲሳይ አለ፡፡
በድሆች እርሻ ላይ ብዙ ሲሳይ አለ፤ ምሳሌ
13፡23
አለም አገልግሎትንም የተጠማች ነች፡፡ አለም የሚያገለግላት
ካገኘት ለመክፈል የተዘጋጀች ነች፡፡ አለም የማትፈልገው ሳያገለግሏት መጠቀም የሚፈልጉትን ነው፡፡ አለም የማትፈልገው በሚሰጡት አገልግሎት
ላይ ሳይሆን በሚያገኘኙት ጥቅም ላይ የሚያተኩሩትን ሰዎች ነው፡፡ አለም የማትፈልገው ለማገልገል ሳይሆን ለመጠቀም የሚጋደሉትን ሰነፎችን
ነው፡፡
የታካች ሰው ነፍስ ትመኛለች፤ አንዳችም አታገኝም፤ የትጉ ነፍስ ግን ትጠግባለች። ምሳሌ 13፡4
ካልሰራህ ካልተጋህ ድህነት ወደቤትህ እና ወደኑሮህ
ለመግባት አይደራደርም፡፡ ድህነት የሰነፍ ሰው ህይወት ውስጥ ለመግባት ፈቃድ አይጠይቅም፡፡ ድህነት የሚመጣው እንደ ወንበዴ በግድ
ነው፡፡ ትንሽ መዘናጋት ትንሽ በስራ ጊዜ ማረፍ ድህነትን ይጠራዋል፡፡
አንተ ታካች፥ ወደ ገብረ ጕንዳን ሂድ፥ መንገድዋንም ተመልክተህ ጠቢብ ሁን። አለቃና አዛዥ ገዢም ሳይኖራት፤ መብልዋን በበጋ ታሰናዳለች፥ መኖዋንም በመከር ትሰበስባለች። አንተ ታካች፥ እስከ መቼ ትተኛለህ? ከእንቅልፍህስ መቼ ትነሣለህ?
ጥቂት ትተኛለህ፥ ጥቂት ታንቀላፋለህ፥ ትተኛም ዘንድ ጥቂት እጅህን ታጥፋለህ፤ እንግዲህ ድህነትህ እንደ ወንበዴ፥ ችጋርህም ሰይፍ እንደ ታጠቀ ሰው ይመጣብሃል። ምሳሌ 6፡6-11
ሰነፍ
ሰው የማይሰራ ሰው ብቻ አይደለም፡፡ ሰነግፍ ሰው ስራውን እውቆ የማይሰራ ሰው ነው፡፡ ሰነፍ ሰው ሁሌ ቀስቃሽ የሚፈልግ ሰው ነው፡፡
ሰነፍ ሰው ሁሌ አበረታች የሚፈልግ ሰው ነው፡፡ ሰነፍ ሰው በራሱ ለመስራርት ለመትጋት መንሳሳት የሜለው ሰው ነው፡፡ ትጉህ ሰው
የሚሰራ ብቻ አይደለም ትጉህ ሰው ነገሮችን በራሱ አነሳሽነት የሚይሰራ ሰው ነው፡፡ ትጉህ ሰው ለመስራት የሰውን ጉትጎታ የማይፈልግ
ሰው ነው፡፡ ትጉህ ሰው ሸክም ያለው ሰው ነው፡፡ ትጉህ ሰው ሸክሙ የማያስተኛው ሰው ነው፡፡ ሰነፍ ሰው ገብረጉንዳን በራሱ አነሳሽነት
የሚያስፈልገውን ሁሉ በትጋት ይሰራል፡፡
አለም
ትጉህን ሰው ታከብራለች፡፡ አለም ሰነፍን አታከብርም፡፡ አለም ለትጉህ ሰው ቦታ አላት፡፡ አለም ሰነፍን ሰው ጥላ ነው የምትሄደው፡፡
አለም ሰነፍን ትንቃለች፡፡
በሥራው
የቀጠፈ ሰውን አይተሃልን? በነገሥታት ፊት ይቆማል፤ በተዋረዱም ሰዎች ፊት አይቆምም። ምሳሌ 22፡29
ሰነፍ
ሰው ከመጥቀም ይልቅ የላከውን ሰው ያማርራል ይጎዳል፡፡
ሆምጣጤ
ጥርስን፥ ጢስም ዓይንን እንደሚጐዳ፥ እንዲሁም ታካች ለላኩት። ምሳሌ 10፡26
እንዲሁ
በመቄዶንያ ሁሉ ላሉት ወንድሞች ሁሉ ታደርጋላችሁና። ነገር ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ከፊት ይልቅ ልትበዙ፥ በጸጥታም ትኖሩ ዘንድ ልትቀኑ፥
የራሳችሁንም ጉዳይ ልትጠነቀቁ፥ እንዳዘዝናችሁም፥ በውጭ ባሉት ዘንድ በአገባብ እንድትመላለሱ፥ አንዳችም እንዳያስፈልጋችሁ በእጃችሁ
ልትሠሩ እንለምናችኋለን። 1ኛ ተሰሎንቄ 4፡10-12
ለተጨማሪ
ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ
መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ
#ጌታ #ትጋት #ስራ #መድከም #ጕንዳን #ሸክም #ጥሪ #አላማ #ግብ #መሪ #ፀጋ #የሚያስችልሃይል #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #አቢይ #አቢይዋቁማ
#አቢይዋቁማዲንሳ #ትህትና #ልብ #እምነት
No comments:
Post a Comment