እንዲህም
አላቸው፦ ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ። ያመነ የተጠመቀም ይድናል፥ ያላመነ ግን ይፈረድበታል። ማርቆስ 16፡15-16
እኛ
ሁላችን በጨለማ በነበርነበት ጊዜ ኢየሱስ ወደምድር የመጣው ወንጌልን ሊሰብክና በጨለማ ያሉትን ከእስራት ሊያወጣ ነው፡፡
ከዚያ
ዘመን ጀምሮ ኢየሱስ፦ መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ እያለ ይሰብክ ጀመር። ማቴዎስ 4፡17
አሰብ
እኔን እንደላከኝ እንደሂ እልካችሃለሁ ይላ ኢየሰስ ፡፡
ወደ
ዓለም እንደ ላክኸኝ እንዲሁ እኔ ወደ ዓለም ላክኋቸው፤ ዮሃንስ 17፡18
እግዚአብሄ
መንፈሱን የሰጠን በህይወትና ምሳሌነትና በቃል ወንጌልን እንድንሰብክ ነው፡፡
ኢየሱስም
ዳግመኛ፦ ሰላም ለእናንተ ይሁን፤ አብ እንደ ላከኝ እኔ ደግሞ እልካችኋለሁ አላቸው። ይህንም ብሎ እፍ አለባቸውና፦ መንፈስ
ቅዱስን ተቀበሉ። ዮሃንስ 20፡21-22
ኢየሱስ
ያለውን ስልጣን ሁሉ ትቶልን የሄደው ወንጌልን እንድንሰብክና ሰዎችን ከጨለማ እንድንታደግ ነው፡፡
ኢየሱስም
ቀረበና እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፦ ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጠኝ። እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ። ማቴዎስ 28፡18-20
ለተጨማሪ
ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ
መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#እምነት
#ወንጌል #ስብከት #ቃል #ዝራ #የምድርጨው #የአለምብርሃን #የአመፃገንዘብ #የእግዚአብሄርሃይል #መንፈስቅዱስ #ቃሉንመስማት #እወጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment