ክርስቶስ በፍቅር ለእኛ መዳን እና መለወጥ የባሪያን መልክ ያዘ፡፡ ክርስቶስ በፍቅር ለመስቀል ሞት እንኳን የታዘዘ ሆነ፡፡
ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ፥ በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፥ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ። ፊልጵስዩስ ሰዎች 2፡7-8
ክርስቶስ የፍቅርን ምሳሌ ትቶልናል፡፡ ክርስቶስ እንደወደደን በፍቅር ልንመላለስ ይገባል፡፡
ክርስቶስም ደግሞ እንደ ወደዳችሁ ለእግዚአብሔርም የመዓዛ ሽታ የሚሆንን መባንና መሥዋዕትን አድርጎ ስለ እናንተ ራሱን አሳልፎ እንደ ሰጠ በፍቅር ተመላለሱ። ኤፌሶን 5፡2
ክርስቶስ ራሱን አሳልፎ እንደሰጠን እኛም ስለወንድሞቻችን ራሳችንን አሳልፈን ልንሰጥ ይገባል፡፡
እርሱ ስለ እኛ ነፍሱን አሳልፎ ሰጥቶአልና በዚህ ፍቅርን አውቀናል፤ እኛም ስለ ወንድሞቻችን ነፍሳችንን አሳልፈን እንድንሰጥ ይገባናል። 1ኛ ዮሐንስ 3፡16
ክርስቶስ እንደወደደን እርስ በእርሳችን ልንዋደድ ይገባል፡፡
እርስ በርሳችሁ ትዋደዱ ዘንድ፥ እንደ ወደድኋችሁ እናንተ ደግሞ እርስ በርሳችሁ ትዋደዱ ዘንድ አዲስ ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ። ዮሃንስ 13፡34
ጳውሎስ ለክርስቶስ ቤተክርስትያን አገልግሎት በፍቅር በሙሉ ፈቃደኝነት ራሱን ባሪያ አድርጎ ሰጠ፡፡
ሐዋርያ ሊሆን የተጠራ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ጳውሎስ በነቢያቱ አፍ በቅዱሳን መጻሕፍት አስቀድሞ ተስፋ ለሰጠው ለእግዚአብሔር ወንጌል ተለየ። ሮሜ 1፡1-2
በታላቅ ፍቅር ተወደናል፡፡ እርሱ እንደወደደን እርስ በእርሳችን ልንዋደድ ይገባናል፡፡
እኔ እንደ ወደድኋችሁ እርስ በርሳችሁ ትዋደዱ ዘንድ ትእዛዜ ይህች ናት። ነፍሱን ስለ ወዳጆቹ ከመስጠት ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም። ዮሃንስ 15፡12-13
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ፋሲካ #ትንሳኤ #ስቅለት #በዓል #መስዋእት #ቤዛነት #መቤዠት #የሚበልጥ #ፍቅር #ተስፋ #ደስታ #መስዋእት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #ብርሃን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #የዋህነት #ንፁህ
No comments:
Post a Comment