እንግዲህ
ሁልጊዜ ታምነን፥ በእምነት እንጂ በማየት አንመላለስምና 2ኛ ቆሮንቶስ 5፡6-7
እምነት የእግዚአብሄርን ቃል እውነት ነው ብሎ
መቀበል ነው፡፡ እምነት እግዚአብሄርን እንደቃሉ መጠበቅ ነው፡፡ እምነት እግዚአብሄርን እንደቃሉ መያዝ ነው፡፡ እምነት እንደቃሉ
ማሰብ እንደቃሉ መናገርና እንደቃሉ ማድረግ ነው፡፡
እግዚአብሄር መንፈስ ነው፡፡ እግዚአብሄር በአይን
አይታይም፡፡ በአይን የማይታየውን እግዚአብሄርን ለማየት እምነት ይጠይቃል፡፡ በአይን የማየታየውን የእግዚአብሄርን መንግስት ለማየት
እምነት ይጠይቃል፡፡ በአይን የማይታየው የእግዚአብሄር መንግስት ውስጥ ለመግባት እምነት ይጠይቃል፡፡ በአይን በማይታየው በእግዚአብሄር
መንግስት ውስጥ ለመስራት እምነት ይጠይቃል፡፡
ወደ ማይታየው እግዚአብሄር ለመቅረብ እምነት ይጠይቃል፡፡
ወደ እግዚአብሄር ቀርበን እንድን ነገር ለማስፈፀም እምነት ይጠይቃል፡፡ በአይን ከማይታየው ከእግዚአብሄር ለመቀበል እምነት ይጠይቃል፡፡
ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር
የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና። ዕብራውያን 11፡6
እምነት የሚመጣው የእግዚአብሄርን ቃል ከመስማት
ነው፡፡ እግዞአብሄን የሚያሳየን የእግዚአብሄር ቃል ነው፡፡ የእግዚአብሄርን መንግስት የሚያሳየን የእግዚአብሄር ቃል ነው፡፡ የእግዚአብሄርን
አሰራር የሚያሳየን የእግዚአብሄር ቃል ነው፡፡
የማይታየውን አለም እይታ የምናገኘው በእግዚአብሄር
ቃል በኩል ነው፡፡ የማይታየውን አለም ለማየት ብርሃን የምናገኘው እግዚአብሄር ቃል ብቻ ነው፡፡
እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው። ሮሜ 10፡17
እምነት
በእግዚአብሄር መንግስት ውስጥ ያለውን ማየት ብቻ አይደለም፡፡ እምነት በአካባቢያችን ያለው ሁኔታ አለማየት ነው፡፡ እምነት በእግዚአብሄር
ቃል ውስጥ ያለውን እውነት መከተል ብቻ አይደለም፡፡ እምነት በአካባቢያችን ያለውን ከእግዚአብሄር ቃል ተቃራኒ የሚናገረውን ሁኔታን
አለመከተል ነው፡፡ እምነት በእግዚአብሄር ቃል ውስጥ ያለውን እውነት መቀበል ብቻ አይደለም፡፡ እምነት በአካባቢያችን ያለውን ከእግዚአብሄር
ቃል ተቃራኒ የሚናገረውን ሁኔታን አለመቀበል ነው፡፡
የማይታየውን እንጂ የሚታየውን ባንመለከት፥ ቀላል የሆነ የጊዜው መከራችን የክብርን የዘላለም ብዛት ከሁሉ መጠን ይልቅ ያደርግልናልና፤ የሚታየው የጊዜው ነውና፥ የማይታየው ግን የዘላለም ነው። 2ኛ ቆሮንቶስ 4፡17-18
ለተጨማሪ ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት
#ልብ #ማየት
###ማመን #ቃል #መናገር #አማርኛ #ስብከት
#መዳን #መፅሃፍቅዱስ
#ማሰላሰል #ማድረግ
#ሁሉይቻላል #ደስታ
#አቢይ #አቢይዋቁማ
#አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት
#መሪ
No comments:
Post a Comment