ሁልጊዜ ደስ ይበላችሁ፤ ሳታቋርጡ ጸልዩ፤ በሁሉ አመስግኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና። 1ኛ ተሰሎንቄ 5፡16-18
እግዚአብሄር ለክብሩ ፈጥሮናል፡፡ እግዚአብሄር እኛን ከመፍጠሩ በፊት በምድር ላይ እንድናደርግለት የፈለገው ፈቃድ ነበረው፡፡ የራሳችንን ፍላጎት ሳይሆን ፈቃዱን በምድር ላይ እንድናደርግ እግዚአብሄር ሰርቶናል፡፡
ሰዎች ሁልጊዜ የእግዚአብሄርን ፈቃድ ለማወቅ ይፈልጋሉ፡፡ ይህ የእግዚአብሄር ፈቃድ ይሆንን ብለው ያስባሉ ይጠይቃሉ፡፡
አእምሮዋችንን በእግዚአብሄር ቃል እንድናድስ የታዘዝነው በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው የእግዚአብሄርን ፈቃድ እንድንለይ ነው፡፡
የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ። ሮሜ 12፡2
በግልፅ የእግዚአብሄር ፈቃድ እንደሆኑ በመፅሃፍ ቅዱሳችን ከተጠቀሱት ነገሮች መካከል እነዚህ ሶስቱ ይገኙበታል፡፡
ሁልጊዜ ደስ ይበላችሁ፤
በነገሮች ብናዝንም በጌታ ደስ እንዲለን የእግዚአብሄርን ፈቃድ እንደሆነ መፅሃፍ ቅዱስ ያስተምረናል፡፡ ሁኔታዎች ቢያሳዝኑንም በጌታ ግን ሁልጊዜ ደስ እንድንሰኝ የእግዚአብሄር ቃል ያዛል፡፡
ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ፤ ደግሜ እላለሁ፥ ደስ ይበላችሁ። ፊልጵስዩስ 4፡6
ሳታቋርጡ ጸልዩ፤
የእግዚአብሄር ልጆች ነን፡፡ ወደእግዚአብሄር መፀለይ እግዚአብሄርን መስማት ከእግዚአብሄር ጋር መነጋገር የእለት ተእለት ተግባራችን ነው፡፡
ጌታ ቅርብ ነው። በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ። ፊልጵስዩስ 4፡6
በሁሉ አመስግኑ፤
እግዚአብሄር መልካም አምላክ ነው፡፡ አምላካችን እግዚአብሄር በእርሱ ዘንድ ምንም ክፉ የሌለበት ሁለንተናው መልካም አምላክ ነው፡፡ እግዚአብሄር ክፉውን ነገር እንኳን ለመልካም የሚለውጥ አምላክ ነው፡
እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን። ሮሜ 8፡28
በምንም ሁኔታ ውስጥ ብናልፍ እግዚአብሄርን ላለማመስገን ምንም ምክኒያት የለንም፡፡ ሰው እነዚህን በማድረግ አይሳሳትም፡፡ ሰው ግን እነዚህን ባለማድረግ ይሳሳታል፡፡
ሁልጊዜ ደስ ይበላችሁ፤ ሳታቋርጡ ጸልዩ፤ በሁሉ አመስግኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና። 1ኛ ተሰሎንቄ 5፡16-18
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #ሳታቋርጡጸልዩ #ሁልጊዜደስይበላችሁ #በሁሉአመስግኑ #የእግዚአብሔርፈቃድ #በክርስቶስ #መሪነት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መጋቢ #እምነት #ተስፋ #ፍቅር #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ
No comments:
Post a Comment