ደግሞ
የእግዚአብሔር ቃል። ኤርምያስ ሆይ፥ ምን ታያለህ? እያለ ወደ እኔ መጣ። እኔም። የለውዝ በትር አያለሁ አልሁ። እግዚአብሔርም፦ እፈጽመው ዘንድ በቃሌ እተጋለሁና መልካም አይተሃል አለኝ። ኤርሚያስ 1፡11-12
እግዚአብሄር
የፈጠረን ለአላማው ነው፡፡ እግዚአብሄር የፈጠረን በክብሩ ነው፡፡ እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረው ከእርሱ ጋር አብሮ እንዲሰራ ነው፡፡
እግዚአብሄር የፈጠረን ለአብሮ ሰራተኝነት ነው፡፡
የእግዚአብሔር
እርሻ ናችሁ፤ የእግዚአብሔር ሕንፃ ናችሁ፤ ከእርሱ ጋር አብረን የምንሠራ ነንና። 1ኛ ቆሮንቶስ 3፡9
አብሮን
ሊሰራ ከሚፈልገው ከእግዚአብሄር ጋር ተስማምተን አብረን መስራት የምንችለው እርሱ የሚያየውን ስናይ ብቻ ነው፡፡ ሰው እግዚአብሄር
የሚሰራውን ማየት ካልቻለ በስተቀር ከእግዚአብሄር ጋር አብሮ ሊሰራ አይችልም፡፡
አብሮት
የሚሰራውን ሰው እርሱ የሚያየውን አብሮ እንዲያይ እግዚአብሄር የሚፈልገው ለዚህ ነው፡፡
እግዚአብሄር
የሚሰራውን ማየት ካልቻልን በራሳችን ብቻችንን ሰርተን ውጤት ላይ መድረስ እንችልም፡፡ እግዚአብሄር የሚሰራውን ማየት ካልቻልን ከእግዚአብሄር
ጋር አብረን ልንሰራ አንችልም፡፡ አግዚአብሄር ሲሰራ ካላየን ከእርሱ ጋር ተባብረን ፍሬያማ መሆን አንችልም፡፡
ኢየሱስ
በምድር በነበረ ጊዜ አብ የሚሰራውን ያይ አብሮም ይሰራ ነበር፡፡ አብ የሚሰራወነ ያይና ከእርሱ ሃር ይተበናበር ስለነበረ ኢየሱስ
በምድር ላይ በአገልግሎቱ ስኬታማ ነበር፡፡
ኢየሱስ
ግን፦ አባቴ እስከ ዛሬ ይሠራል እኔም ደግሞ እሠራለሁ ብሎ መለሰላቸው። ዮሃንስ 5፡17
ስለዚህ
ኢየሱስ መለሰ እንዲህም አላቸው፦ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብ ሲያደርግ ያየውን ነው እንጂ ወልድ ከራሱ ሊያደርግ ምንም አይችልም፤
ያ የሚያደርገውን ሁሉ ወልድ ደግሞ ይህን እንዲሁ ያደርጋልና። አብ ወልድን ይወዳልና፥ የሚያደርገውንም ሁሉ ያሳየዋል፤ እናንተም
ትደነቁ ዘንድ ከዚህ የሚበልጥ ሥራ ያሳየዋል። ዮሃንስ 5፡19-20
አሁንም
እግዚአብሄር በየጊዜው የሚጠይቀው ይህንኑ ጥያቄ ነው፡፡
አብሮን
ሊሰራ ሲፈልግ ምን ታያለህ ይለናል፡፡ ውጤታማ እንድንሆን ስለሚፈለግ ምን እንዳየን ማወቅ ይፈልጋል፡፡ ምክኒያቱም ባየነው መጠን
ብቻ ነው አብረነው የምንሰራውና ውጤታማ የምንሆነው፡፡
የእግዚአብሄርን
መንግስት እና የእግዚአብሄርን አሰራር የምናየው በቃሉ ነው፡፡
ቃሉን
በሚገባ ካየን እግዚአብሄርን እናየዋለን፡፡ ቃሉን ካየን የእግዚአብሄርን መንግስት አሰራር እንረዳለን፡፡ ቃሉን ካየን እግዚአብሄር
ሲሰራ እናየዋለን አብረንም በመስራት ውጤታማ መሆን እንችላለን፡፡
እግዚአብሄር
በህይወታችን የሚሰራውን ካየን እግዚአብሄር በህይወታችን ሊፈፅም ያሰበውን አላማ በሚገባ መፈፀም እንችላለን፡፡ እግዚአብሄር በህይወታችን
የሚሰራውን ካየን ከእርሱ ጋር ተባበረን ስኬታማ መሆን እንችላለን፡፡
ደግሞ
የእግዚአብሔር ቃል። ኤርምያስ ሆይ፥ ምን ታያለህ? እያለ ወደ እኔ መጣ። እኔም። የለውዝ በትር አያለሁ አልሁ። እግዚአብሔርም፦
እፈጽመው ዘንድ በቃሌ እተጋለሁና መልካም አይተሃል አለኝ። ኤርሚያስ 1፡11-12
ፀሎት
እግዚአብሄር
ሆይ ስለአባትነትህ ሁሉ አመሰግንሃለሁ፡፡ እግዚአብሄር ሆይ አይኖቼን ክፈት፡፡ እግዚአብሄር ሆይ አንተ በክርስቶስ ያደረክልኝን ሁሉ መረዳት እንድችል የጥበብና የመገለጥን
መንፈስ ስጠኝ፡፡ አንተ በህይወቴ የምታየውን ማየት አችል ዘንድ አይኖቼን ክፈት፡፡ አንተ የምትሰራወነ አይቼ
እተባበርክህ ዘንድ አይኔን
ክፈት፡፡ ከአንት ጋር በትክክል መራመድ እንድችል አንተ ስለህይወቴ የምታየውን ሁሉ ልይ፡፡ አይኔን ስለምትከፍት ስራህን በህይወቴ ሰለማይ አመሰግንሃለሁ፡፡ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን
ለተጨማሪ
ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ
መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ
#ጌታ #መሪነት #አይን #እይታ #ተኣምራት #እድል #ዘመን #እድል #ዋጁ #ጥበብ #መተርጎም #ይሳኮር #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #እምነት #ምሪት #ድምፅ #ጌታ #ሰላም #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ
No comments:
Post a Comment