እንደ
ኢየሱስ ክርስቶስ በጎ ወታደር ሆነህ፥ አብረኸኝ መከራ ተቀበል። የሚዘምተው ሁሉ ለጦር ያስከተተውን ደስ ያሰኝ ዘንድ ትዳር በሚገኝበት ንግድ ራሱን አያጠላልፍም። 2ኛ ጢሞቴዎስ 2፡3-4
ወታደር የቆረጠ ሰው ነው፡፡ ወታደር ራሱን ለወታደራዊ
ጥብቅ ስርአት ለማስገዛት የወሰነ ሰው ነው፡፡ ወታደር ለስላሳ ሰው አይደለም፡፡ ወታደር ጠንካራ
ሰው ነው፡፡ ወታደር ከወታደርነት ውጭ ያለውንም የሲቪል ኑሮ ለመኖር ጨካኝ ሰው ነው፡፡ ወታደር የሚበላውንና የሚጠጣውን አይመርጥም፡፡
ወታደር የግሉ የሆነ ፍላጎት የለውም፡፡ ወታደር
የአዛዡን ትእዛዝ ለመፈፀም የተዘጋጀ ነው፡፡
ወታደር መከራን የሚፈራ ሰው አይደለም፡፡ ወታደር
አልጋ በአልጋ የሆነን የተመቻቸን ኑሮ ብቻ የሚፈልግ ሰው አይደለም፡፡ ወታደር መከራንና አስቸጋሪን ነገር ለመጋፈጥ የወሰነ ሰው
ነው፡፡
የወታደር አላማ ራሱን ማስደሰት አይደለም፡፡ የወታደር
አላማ ነፍሱን ማስደሰት አይደለም፡፡ የወታደር የመጀመሪያው አላው ያዘመተውን ሰው ማስደሰት ነው፡፡ ወታደር የሚረካው ያዘመተው አዛዥ
ሲረካ ነው፡፡ ወታደር አዛዡን ከማስደሰት ውጭ ሌላ አላ የለውም፡፡
ወታደር አዛዡ የማይረካበትን ነገር ሁሉ ይንቃል፡፡
ወታደር አዛዡ የማይፈልገውን ነገር ሁሉ አይፈልግም፡፡
እንዲሁም ክርስትያን ኢየሱስን ለማስደሰት ራሱን
የሰጠ ሰው ነው፡፡
ክርስትያን ኢየሱስን ለማስደስት መከራን ይመርጣል፡፡
ሙሴ ካደገ በኋላ የፈርዖን የልጅ ልጅ እንዳይባል
በእምነት እምቢ አለ፤ ከግብፅም ብዙ ገንዘብ ይልቅ ስለ ክርስቶስ መነቀፍ እጅግ የሚበልጥ ባለ ጠግነት እንዲሆን አስቦአልና ለጊዜው በኃጢአት ከሚገኝ ደስታ ይልቅ ከእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር መከራ መቀበልን መረጠ፤ ብድራቱን ትኵር ብሎ ተመልክቶአልና። ዕብራውያን 11፡24-26
የእግዚአብሄርን ሃሳብ ለመከተል ክርስቶስ ሰዎች
የሚያከብሩትን በህይወታቸው ከሚሆንባቸው ሞትን የሚመርጡትን ነውርን ናቀ፡፡የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት
እንሩጥ፤ እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና።ዕብራውያን 12፡1-2
ክርስትያን ክርስቶስን ለመከተል ሰዎች የሚያከብሩትን
ነገር ይንቃል፡፡ ክርስትያን ክርስቶስን ለመከተል ስደትንና መከራን ይንቃል፡፡
ክርስትያን ክርስቶስን በአስተሳሰቡ ፣ በአነጋገሩና
በአደራረጉ ለማክበር የቆረጠ ነው፡፡ ክርስትያን ክርስቶስን ለመከተል የሚመጣበትን ማንኛውም መከራ ለመቀበል የቆረጠ ነው፡፡
እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ በጎ ወታደር ሆነህ፥ አብረኸኝ
መከራ ተቀበል። የሚዘምተው ሁሉ ለጦር ያስከተተውን ደስ ያሰኝ ዘንድ ትዳር በሚገኝበት ንግድ ራሱን አያጠላልፍም። 2ኛ ጢሞቴዎስ
2፡3-4
ለተጨማሪ ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #ክብር
#ትዳር #ንግድ #ወታደር #ዘማች #መዋረድ #መከራ
#ፈተና #መፅናት
#መታገስ #አማርኛ
#ስብከት #መዳን
#መፅሃፍቅዱስ #ብፅእና
#እምነት #አንድነት
#ፀጋ
#አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment