Popular Posts

Follow by Email

Wednesday, April 18, 2018

የእግዚአብሔር ችሎታ

ፀጋን ስናስብ ብዙ ጊዜ ወደ አእችምሮዋችን የሚመጣው ነፃ ስጦታ መሆኑ ነው፡፡ እውነት ነው ፀጋ ነፃ ስጦታ ነው፡፡ ፀጋ የሚያስችል ሃይል ነው፡፡ ፀጋ ብቃት ነው፡፡ ፀጋ አንድን ነገር ለማድረግ የሚያስፈልገንን ሃይል ማግኘት ነው፡፡
ሃጢያት የራሱ የሆነ ሃይል አለው፡፡ ካለ እግዚአብሄር ፀጋ ሃጢያትን መካድ አንችልም፡፡ ካለ እግዚአብሄር ፀጋ አለማዊ ምኞትን መካድ አንብችልም፡፡ ሃጢያት የራሱ የሆነ ካለ እግዚአብሄር ፀጋ ሃይማኖት ሃይማኖት ጨዋታ እንጫወታለን እንጂ ክርስትናን አንኖርም፡፡ ህይወታችን ከተለወጠ በእግዚአብሄር ፀጋ ብቻ ነው፡፡
ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጦአልና፤ ይህም ጸጋ፥ ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞት ክደን፥ የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እየጠበቅን፥ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል፤ ቲቶ 2፡11-13
ካለ እግዚአብሄር ፀጋ ውጫዊ ነገራችንን እያስተካከልን በማስመሰል እንኖራለን እንጂ እውነተኛ የህይወት ለውጥ አይኖርም፡፡ እውነተኛ የልብ ለውጥ የሚመጣው በእግዚአብሄር ፀጋ ነው፡፡
ልባችሁ በጸጋ ቢጸና መልካም ነው እንጂ በመብል አይደለም፤ በዚህ የሚሠሩባት አልተጠቀሙምና። ዕብራውያን 13፡9
የእግዚአብሄር ፀጋ ከጎደለ ርክሰት ይመጣል፡፡ የእግዚአብሄር ፀጋ ከጎደለ የህይወት ድካም ይመጣል፡፡ የእግዚአብሄር ፀጋ ከጎደለ የህይወት ድካም ይመጣል፡፡  
የእግዚአብሔር ጸጋ ለማንም እንዳይጎድለው፥ ብዙዎቹም የሚረክሱበት አንድ መራራ ሥር ወደ ላይ በቅሎ እንዳያስጨንቅ፥ ሴሰኛም የሚሆን እንዳይገኝ፥ ዕብራውያን 12፡15
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #መሪ #ፀጋ #የሚያስችልሃይል #ብቃት #የእግዚአብሄርችሎታ #የእግዚአብሄርሃይል #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ትጋት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #ፅድቅ #እግዚአብሄርንመምሰል #ራስንመግዛት #ልብ

No comments:

Post a Comment