Popular Posts

Sunday, April 15, 2018

እምነትና ፍርሃት

ከእግዚአብሄር ጋር ላለን የሰመረ ግንኙነት እምነት ወሳኝ ነው፡፡ እንዲያውም ካለእምነት እግዚአብሄርን ደስ ማሰኘት አይቻልም፡፡
ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና። ዕብራውያን 11፡6
አንዱ የእምነት ጠላት ደግሞ ፍርሃት ነው፡፡ ፍርሃትን ከሰማነው ከእምነት ጉዞ ልናቋርጥ እንችላለን፡፡ ፍርሃትን ከሰማነው እግዚአብሄር በህይወታችን ያስቀመጠውን አላማ ሳናከናውን እንቀራለን፡፡
እምነት የእግዚአብሄርን ቃል እንድንሰማና እንድንከተል ያደርጋል፡፡ ፍርሃት ደግሞ የእግዚአብሄርን ቃል እንዳንሰማና እንዳንከተል ያደርጋል፡፡
እምነት አለን ማለት ግን ከፍርሃት ስሜት ነፃ እንሆናለን ማለት አይደለም፡፡ የፍርሃት ስሜት የማይኖረን ወደሰማይ ስንሄድ ብቻ ነው፡፡ በምድር ላይ ይብዛም ይነስም የፍርሃት ስሜት አለ፡፡
የፍርሃት ስሜት አለን ማለት ግን እምነት የለንም ማለት አይደለም፡፡ የፍርሃት ስሜት አለን ማለት እንዲያውም የማመን እድሉ አለን ማለት ነው፡፡ የፍርሃት ስሜት አለን ማለት እንዲያውም እምነት አለን ማለት ነው፡፡ የፍርሃት ስሜት አለን ማለት እምነታችንን ፍርሃት እየተፈታተነው ነው ማለት ነው፡፡ ፍርሃት የሚመጣው የሚያምንን ሰው ለማስቆም ነው፡፡
ፍርሃት የሚያምንን ሰው ካላስቆመ በከንቱ ይደክማል፡፡ ፍርሃት የሚያምንን ሰው ካላስቆመ ስኬታማ አይደለም፡፡ ፍርሃት የሚያምንን ሰው ካላስቆመ አይከናወንለትም፡፡
የፍርሃትን ስሜት ካልተከተልነው በእምነታችን አሸናፊ እንሆናለን፡፡ ደፋር የሚባለው ሰው ምንም የፍርሃት ስሜት የማይሰማው ሰው አይደለም፡፡ ደፋር የሚባለው እንዲያውም በጣም የሚያስፈራ ነገር ውስጥ የሚያልፍ ሰው ነው፡፡ ደፋር የፍርሃት ስሜት እንዳይገዛው የሚያደርግ ሰው ነው፡፡ ደፋር ሰው በፍርሃት ስሜት የማይሸነፍ ሰው ነው፡፡ ደፋር ስው የፍርሃት ስሜት የማይወሰደ ሰው ነው፡፡ ደፋር ሰው ፍርሃትን ሰምቶ ከእምነት ጊዞ የማይቆም ነው፡፡
እንግዲህ ታላቅ ብድራት ያለውን ድፍረታችሁን አትጣሉ። ዕብራውያን 10፡35
ኢየሱስ ግን የተናገሩትን ቃል አድምጦ ለምኵራቡ አለቃ፦ እመን ብቻ እንጂ አትፍራ አለው። ማርቆስ 5፡36
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #ልብ #ማመን #ቃል #መናገር #ስሜት #ፍርሃት #ሁኔታ #አካባቢ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #አለማመን #ጥርጥር #ሁሉይቻላል #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት

No comments:

Post a Comment