አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው
ሉቃስ 23፡34
ኢየሱስ ሲሰቀል ያሳየው ትህትና ልዩ ነበር፡፡
ኢየሱስ የእርሱ መሰቀልና መሰቃየት ሳያሳስበው ለሰቀሉት ሰዎች ይቅርታ ማግኘት ይበልጥ ያሳስበው ነበር፡፡
አሁንም ሰዎች ሲበድሉን እንድንራራላቸው ያስፈልጋል፡፡
ሰዎች ሲበድሉን እኛን እግዚአብሄር ይክሰናል፡፡ በዳይ ሰዎች ግን በእግዚአብሄር ይገሰፃሉ እንጂ በእግዚአብሄር አይካሱም፡፡
እንግዲህ ፈጽሞ የእርስ በርስ ሙግት እንዳለባችሁ በእናንተ ጉድለት ነው። ብትበደሉ አይሻልምን? ብትታለሉስ አይሻልምን? 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ 6፡7
የሚበድሉ ሰዎፖች ሰላም የላቸውም፡፡ የሚበድሉ
ሰዎች እረፍት የላቸውም፡፡ የሚበድሉ ሰዎች እርካታ የላቸውም፡፡
ሰው ካለ ምክኒያት አይበድልም፡፡ ሰው ካልቸገረው ሌላውን ሰው በመበደል ከእግዚአብሄር
ጋር አይጣላም፡፡ ሰው የቀናው መንገድ ካልጠፋው በስተቀር ሰውን አይበድልም፡፡ ሰው ካልተታለለ በስተቀር ሌላውን ሰው አይበድልም፡፡
ሰው ካልተሸወደ በስተቀር በትክክለኛ አእምሮ ሌላው ሰውን በመበደል እግዚአብሄርን አይበድልም፡፡
የሚበድሉ ሰዎች ርህራሄ ሊደረግላቸው ያስፈልጋቸዋል፡፡ የሚበድሉ ሰዎች የሚታዘንናለቸው
ምስኪን ሰዎች ናቸው፡፡ የሚበድሉ ሰዎች ሳንረግማቸው ተረግመዋል፡፡ የሚበድሉ ሰዎች ሳንበድላቸው ራሳቸውን በድለዋል፡፡
ለሚበድሉን ሰዎች መራራት የሚከብደን የተጠቀሙ
ስለሚመስለን ነው፡፡ የሚበድል ሰው ይጎዳል እንጂ አይጠቀምም፡፡
ለሚበድሉ ሰዎች እንራራላቸውን እንዘንላቸው ማለት
ግን አንጋፈጣቸው ትክክለኛውን መንገድ አናሳያቸው ማለት አይደለም፡፡ ለሚበድሉ ሰዎች እንፀልይላቸው ማለት እንመልሳቸው ማለት እንጂ
እናበረታታቸው ማለት በፍፁም አይደለም፡፡ የሚበድሉ ሰዎች እንባርካቸው ማለት ሃይል እንስጣቸው ማለት ሳይሆን በችግር ላይ እርግማን
አንጨምርባቸው ማለት ነው፡፡
የሚያሳድዱአችሁን መርቁ፥ መርቁ እንጂ አትርገሙ። ሮሜ 12፡14
ሰዎች
ሲበድሉ አይጠቀሙም፡፡ በሰዎች መበደል የሚጠቀመው ሰይጣን ነው፡፡ በሰዎች መቆሸሽ የሚጠቀመው ጠላት ነው፡፡ ሰዎች ሰውን ለመበደል
ሰይጣን ሲጠቀምባቸው ይጎዳሉ፡፡
እኔ ግን እላችኋለሁ፥
በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፥ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፥ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፥ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤ ማቴዎስ 5፡44-45
ሰዎችን ይቅር ስንላቸውና ስንታገሳቸው ገንዘባችን
እናደርጋቸዋለን፡፡
ወንድምህም ቢበድልህ፥ ሄደህ አንተና እርሱ ብቻችሁን ሆናችሁ ውቀሰው። ቢሰማህ፥ ወንድምህን ገንዘብ አደረግኸው፤ ማቴዎስ 18፡15
ለተጨማሪ ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #እግዚአብሔር #ይቅርታ #ምህረት
#ፍርድ #ጠላት
#ዲያቢሎስ #ስፍራ
#ኢየሱስ #ጥላቻ
#ትእቢት #መራርነት
#ጌታ #መሪነት
#ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ
#ሰላም #አቢይ
#አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
#እወጃ #መናገር
#ፅናት #ትግስት
#መሪ
No comments:
Post a Comment