በአለም ላይ የተለያዩ ድምፆች አሉ፡፡ በአለም
ላይ መስማት ያለብንና መስማት የሌለብን ድምፆች አሉ፡፡ በአለም ላይ ልንከተለው የሚገባና ልንከተለው የማይገባ ሁኔታ አለ፡፡
ከእግዚአብሄር ቃል የሚገኝ የእግዚአብሄር ድምፅ
አለ፡፡ ሰው ያንን የእግዚአብሄርን ቃል ሲሰማ እምነት ይመጣለታል፡፡ ሰው የእግዚአብሄርን
ቃል ሲሰማ የእግዚአብሄርን መንግስት ማየት ይችላል፡፡ ሰው የእግዚአብሄርን ቃል ሲሰማ የእግዚአብሄርን ፈቃድ ማወቅ ይችላል፡፡ ሰው
የእግዚአብሄርን ቃል ሲሰማ የእግዚአብሄርን መንግስት ሊያይ ይችላል፡፡ ሰው የእግዚአብሄርን ቃል ሲሰማ ከእግዚአብሄር ጋር መኖር
ይችላል፡፡ ሰው የእግዚአብሄርን ቃል ሲሰማ ወደ እግዚአብሄር ሊቀርብ ይችላል፡፡ ሰው የእግዚአብሄርን ቃል ሲሰማ ከእግዚአብሄር ሊቀበል
ይችላል፡፡ ሰው የእግዚአብሄርን ቃል ሲሰማ ከእግዚአብሄር ጋር ሊገናኝ ይችላል፡፡
እምነትም ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ፥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ
ነው። ዕብራውያን 11፡1
ሰው የእግዚአብሄርን ቃል ሲሰማ የእግዚአብሄርን መንግስት ማየት ይችላል፡፡ ሰው
የእግዚአብሄር ቃል ሲሰማ የእግዚአብሄርን መንግስት አሰራር ሊረዳ ይችላል፡፡ ሰው የማይታየውን ማየት የሚችለው በእግዚአብሄር ቃል
ነው፡፡ እምነት የሚመጣው የእግዚአብሄርን ቃል በመስማት ነው፡፡
በአለም ላይ የእግዚአብሄርን ቃል የሚቃረን ሌላ ድምፅ ደግሞ አለ፡፡
ሰይጣን የውሸት አባት ነው፡፡ ሰይጣን በልባችን ያለውን በእግዚአብሄር ቃል በኩል
ያገኘነውን እውነት ለመስረቅ ይመጣል፡፡ ሰይጣን ከእግዚአብሄር ቃል ያገኘነውን እውነት በውሸት ሊያስጥለን ይመጣል፡፡ ሰይጣን እውነቱን
ትተን ውሸቱን እንድናምን ይፈልጋል፡፡ ሰይጣን የማይታየውን ማየት ትተን የሚታየውን በማየት ከእግዚአብሄር በረከት እንድንወድቅ ይፈልጋል፡፡
ሁኔታ የእግዚአብሄርን ቃል ሊቃረን ይችላል፡፡ የሚታየው ነገር ከማይታየው ነገር
ተቃራኒ ሊሆን ይችላል፡፡ የአካባቢያችን ሁኔታ ከምናውቀው ከእግዚአብሄር ቃል ተቃራኒ ሊሆን ይችላል፡፡
የማይታየውን እንጂ የሚታየውን ባንመለከት፥ ቀላል የሆነ የጊዜው መከራችን የክብርን
የዘላለም ብዛት ከሁሉ መጠን ይልቅ ያደርግልናልና፤ የሚታየው የጊዜው ነውና፥ የማይታየው ግን የዘላለም ነው። 2ኛ ቆሮንቶስ 4፡17-18
ስለዚህ ነው የሚታየው ከማይታየው ከእግዚአብሄር ፈቃድ ሲቃረን የሚታየውን ማየት
ትትን የማይታየው የእግዚአብሄ ቃል ላይ ማተኮር ያለብን፡፡
የሚታየው የሚመጣው ከማይታየው ነው፡፡ የሚታየውን የሚገዛው የማይታየው ነው፡፡ የሚታየው
ለማይታየውን ይገዛል፡፡
ዓለሞች በእግዚአብሔር ቃል እንደ ተዘጋጁ፥ ስለዚህም የሚታየው ነገር ከሚታዩት እንዳልሆነ
በእምነት እናስተውላለን። ዕብራውያን 11፡3
የሚታየው ቋሚ አይደለም፡፡ የሚታየው ተለዋዋጭ ነው፡፡ የሚታየው ጊዜያዊ ነው፡፡
የሚታየው ይለወጣል፡፡ የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ የሚታየው ለማይታየው ፈቃድ ይገዛል፡፡
ከእግዚአብሄር ጋር ስኬታማ ለመሆን የማይታየውን እንጂ የሚታየውን አንመልከት፡፡
በእግዚአብሄር ስራ ፍሬያማ ለመሆን በማይታየውን ላይ እንጂ የሚታየው ላይ አናተኩር፡፡ የእግዚአብሄርን ስራ ለመስራት በማይታየው
እንጂ በሚታየው ነገር አንወሰድ፡፡ ከእግዚአብሄር ጋር ያለን ግንኙነት እንዲሰምር የሚታየውን ትተን የማይታየውን እንመልከት፡፡
የማይታየውን እንጂ የሚታየውን ባንመለከት፥ ቀላል የሆነ የጊዜው መከራችን የክብርን
የዘላለም ብዛት ከሁሉ መጠን ይልቅ ያደርግልናልና፤ የሚታየው የጊዜው ነውና፥ የማይታየው ግን የዘላለም ነው። 2ኛ ቆሮንቶስ 4፡17-18
ለተጨማሪ ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #ልብ #ማመን #ማየት #መስማት #የሚታየው #የማይታየው #እንመልከት #አንመልከት #ቃል #መናገር #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ማሰላሰል #ማድረግ #ሁሉይቻላል #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #ፅናት #ትግስት #መሪ
No comments:
Post a Comment