Popular Posts

Follow by Email

Saturday, April 21, 2018

የፀጋ አስተምሮት

ፀጋ በክርስትና ህይወት በጣም አስፈላጊ ነገር ነው፡፡ ፀጋን ካልተረዳን ክርስትናን አንረዳውም፡፡ ፀጋን ከተረዳነው ደግሞ ክርስትና ፍሬያማ ይሆናል፡፡ ክርስትና የሚጀመረው በፀጋ ነው፡፡ ክርስትና የሚጀመረው በነፃ የተሰጠንን የደህንነት ስጦታ በመቀበል ነው፡፡
ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤ ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም። ኤፌሶን 2፡8-9
የእግዚአብሄር ፀጋ በነፃ የተሰጠን የእግዚአብሄር ችሎታ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ፀጋ የእግዚአብሄር ልጆች የሚያደርገን የእግዚአብሄር ሃይል ነው፡፡ የእግዚአብሄር ፀጋ በእግዚአብሄር ልጅነት ስልጣን እንድንመላለስ የሚያደርገን የእግዚአብሄር የሚያስችል ሃይል ነው፡፡
ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤ ዮሃንስ 1፡12
በእግዚአብሄር ልጅነት ደረጃ ኖረን እግዚአብሄርን እንድናስደስት የሚያበቃን የእግዚአብሄር ፀጋ ብቻ ነው፡፡  
በሃይማኖት ብትኖሩ ራሳችሁን መርምሩ፤ ራሳችሁን ፈትኑ፤ ወይስ ምናልባት የማትበቁ ባትሆኑ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ በእናንተ ውስጥ እንዳለ ስለ እናንተ አታውቁምን? 2ኛ ቆሮንቶስ 13፡5
ክርስትና የሚጀምረው ከጠላትነት ልጆች የሚያደርገንን የእግዚአብሄርን ችሎታ በማመን ነው፡፡ ክርስትና የሚጀመረው ለደህንነታችን ሙሉ ዋጋ የከፈለውን ኢየሱስን ለእኛ እንዳደረገው በማመን ነው፡፡
ክርስትና የሚኖረው በፀጋ ነው፡፡ ክርስትና የሚኖረው ራስ ጉልበት አይደለም፡፡ ክርስትና የሚኖረው በራስ እውቀት አይደለም፡፡ ክርስትያ የሚኖረው በራሰ ችሎታ አይደለም፡፡ ክርስትና የሚኖረው በሚያስችል በእግዚአብሄር ፀጋ ነው፡፡ ክርስትና ካለእግዚአብሄር ፀጋ ሃይማኖት ባዶ ነው፡፡ ካለ እግዚአብሄር ሃይል እግዚአብሄርን ሊያስደስት የሚችል ሰው የለም፡፡ ካለ እግዚአብሄር ምሪት እግዚአብሄርን ሊያስደስት የሚችል ሰው የለምም፡፡
ክርስትናም የሚጨረሰው እንዲሁ በፀጋ ነው፡፡
በእግዚአብሄር ፀጋ ጀምረን በራሳችን ጉልበት አንጨርስም፡፡ በመልካም የምንጨርሰው በእግዚአብሄር ጉልበት ብቻ ነው፡፡ በሃይል የምንጨርሰው በእግዚአብሄር ችሎታ ብቻ ነው፡፡ በመልካም የምንጨርሰው በእግዚአብሄር የመንፈስ እርዳታ ብቻ ነው፡፡  ጌታም መልካም፥ አንተ በጎ፥ ታማኝም ባሪያ የሚለን በእምነት እርሱ ላይ በመደገፍ ብቻ እንጂ በራሳችን ሃይልና ጥበበ አይደለም፡፡
ይህን ብቻ ከእናንተ እንድማር እወዳለሁ፤ በሕግ ሥራ ወይም ከእምነት ጋር በሆነ መስማት መንፈስን ተቀበላችሁን? እንዲህን የማታስተውሉ ናችሁ? በመንፈስ ጀምራችሁ አሁን በሥጋ ትፈጽማላችሁን? ገላትያ 3፡2-3
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #መሪ #ፀጋ #የሚያስችልሃይል #ብቃት #የእግዚአብሄርችሎታ #የእግዚአብሄርሃይል #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ትጋት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #ፅድቅ #እግዚአብሄርንመምሰል #ራስንመግዛት #ልብ

No comments:

Post a Comment