Popular Posts

Follow by Email

Sunday, April 8, 2018

ማንም አይቋቋምህም

በሕይወትህ ዕድሜ ሁሉ ማንም አይቋቋምህም፤ ከሙሴ ጋር እንደ ሆንሁ እንዲሁ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ አልጥልህም፥ አልተውህም። ኢያሱ 1:5
እግዚአብሄር ንጉስ ነው፡፡ እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረው እንዲገዛ ነው፡፡
እግዚአብሄር ተልእኮን የሰጠው ሰው ሁሉ እግዚአብሄር ተልእኮን በሰጠው ስፍራ ሁሉ ይገዛል፡፡
እግዚአብሄርን ሊያስቆም የሚችል ሰው እንደሌለ ሁሉ እግዚአብሄር የሰጠውን ተልእኮ ሊያስቆም የሚችል ማምን ሃይል የለም፡፡
ስለዚህ እናንተ ምስክሮቼ ናችሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ እኔም አምላክ ነኝ። ከጥንት ጀምሮ እኔ ነኝ ከእጄም የሚያመልጥ የለም፤ እሠራለሁ፥ የሚከለክልስ ማን ነው? ኢሳያስ 43፡12-13
እግዚአብሄርን እየተከተልነውና እያገለገልነው እኛን ተቃውሞ የሚሳካለት ሰው የለም፡፡ ለእግዚአብሄር እየኖርን እኛን በመቃወም የሚከናወንለት ሰው ከሰማይ በታች የለም፡፡ እግዚአብሄን ሊቋቋመው የሚችል ማነመ እንደሌለ የእግዚአብሄርን ፈቃድ ሊያስቆም የሚችል ሃይል ከሰማይ በታች የለም፡፡
እንግዲህ ስለዚህ ነገር ምን እንላለን? እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ይቃወመናል? ሮሜ 8፡31
በምድር ላይ ሰዎችን የሚያሸነፉ ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ የእግዚአብሄርን ፈቃድ ስንፈፅም ሰዎችን የሚያሸንፉ አሸናፊዎች እኛን ግን ማሸነፍ አይችሉም፡፡ ከእግዚአብሄር ጋረ እየተራመድን ከአሸናፊዎች እንበረታለን፡፡
በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን። ሮሜ 8፡35-38
አምላኩ እንደሆነለት ህዝብ ያለ ህዝብ የለም፡፡ የእግዚአብሄርን ስራ ስንሰራ የሚያቆመን ማንም ስለሌለ እግዚአብሄር ይመስገን፡፡
ነገር ግን በክርስቶስ ሁልጊዜ ድል በመንሣቱ ለሚያዞረን በእኛም በየስፍራው ሁሉ የእውቀቱን ሽታ ለሚገልጥ ለአምላክ ምስጋና ይሁን፤ 2 ቆሮንቶስ 2:14
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እምነት #አይቋቋምህም #አሸናፊ #ድል #ፍቅር #የክርስቶስፍቅር #ስር #መሰረት #ትእዛዝ #መስጠት #ሃሳብ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ልብ #ቸርነት #ትግስት #ፍርሃት #ደስታ #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #መናገር #መውደድ #ትግስት #መሪ

No comments:

Post a Comment