እምነትና ቅንነት አብረው የሚሄዱ ተመሳሳይ ነገሮች
ናቸው፡፡ እምነትና ኩራት አብረው ሊሄዱ የማይችሉ ተቃራኒ ነገሮች ናቸው፡፡
እነሆ፥ ነፍሱ ኰርታለች፥ በውስጡም ቅን አይደለችም፤ ጻድቅ ግን በእምነቱ በሕይወት ይኖራል። ዕንባቆም 2፡4
እምነትና ኩራት አብረው የሚሄዱ ነገሮች አይደሉም፡፡
እምነት ካለ ትምክህት አይኖርም፡፡ ትምክህት ካለ እምነት አይኖርም፡፡ ሰው እግዚአብሄርን ካመነ በምንም ነገር አይመካም፡፡ ሰው
እግዚአብሄርን ለማመን በራስ መተማመንን መጣል አለበት፡፡ ሰው በራሱ ከተማመነ እግዚአብሄርን ሊያምን አይችልም፡፡
ሰው እግዚአብሄርን ለማመን ለእግዚአብሄር ቃል
ቅን መሆን አለበት፡፡ ሰው በእግዚአብሄርን ለማመን የእግዚአብሄርን ቃል እውነት ነው ብሎ በየዋህነት መቀበል አለበት፡፡
ሄዋን ቅንነትዋ ሲበላሽ እምነትዋን አጣች፡፡ ሄዋን
ቅንነትዋን እስከጠበቀች ድረስ እምነትዋን ጠብቃ ነበር፡፡
ነገር ግን እባብ በተንኮሉ ሔዋንን እንዳሳታት፥ አሳባችሁ ተበላሽቶ ለክርስቶስ ከሚሆን ቅንነትና ንጽሕና ምናልባት እንዳይለወጥ ብዬ እፈራለሁ። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11፡3
ሰው ቅን ካልሆነ እግዚአብሄርን ይጠራጠራል፡፡
ሰው ቅን ካልሆነ እግዚአብሄርን ማመን አይችልም፡፡
አንድ መክሊትም የተቀበለው ደግሞ ቀርቦ፦ ጌታ ሆይ፥ ካልዘራህባት የምታጭድ ካልበተንህባትም የምትሰበስብ ጨካኝ ሰው መሆንህን አውቃለሁ፤ ማቴዎስ 25፡24
እምነት ትህትናን ይጠይቃል፡፡ ትሁት የሆነና ራሱን
የሚያዋርድ ሰው ብቻ ነው እግዚአብሄርን አምኖ የሚጠብቀው፡፡ ትእቢተኛ የሆነና በራሱ የሚመካ ሰው እግዚአብሄርን መጠበቅ አይችልም፡፡
በራሱ ለሚመካ ሰው እግዚአብሄርን ማመን ሞኝነት ነው፡፡ እኔ አውቃለሁ የሚል ሰው እግዚአብሄርን ማመን አይችልም፡፡
ሰው እምነቱን ለመጠበቅ ለእግዚአብሄር ያለውን
ቅንነት መጠበቅ አለበት፡፡ ሰው እምነቱን ላለማጣት ለእግዚአብሄር ቃል ያለውን ቅናት ማጣት የለበትም፡፡ ሰው ቅንነቱን ካጣ እግዚአብሄርን
ይጠራጠራል፡፡ የሰው ነፍሱ ከኮራ እግዚአብሄርን ማመን ያቅተዋል፡፡ ሰው ቅንነቱን ካጣ በእግዚአብሄር ሳይሆን በራሱ መደገፍ ይጀምራል፡፡
እነሆ፥ ነፍሱ ኰርታለች፥ በውስጡም ቅን አይደለችም፤
ጻድቅ ግን በእምነቱ በሕይወት ይኖራል። ዕንባቆም 2፡4
ለተጨማሪ ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ትህትና #መዋረድ #ባህሪ
#ዝቅታ #ቅንነት
#ኰርታለች #ቅን #እምነት #ትዕቢት #ትምክህት #መመካት
#ኢየሱስ #ጌታ
#መሪነት #ቤተክርስትያን
#አማርኛ #ስብከት
#መዳን #መፅሃፍቅዱስ
#መጋቢ #እምነት
#ተስፋ #ፍቅር
#ጌታ #ሰላም
#ደስታ #አቢይ
#አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
#እወጃ #መናገር
#ፅናት #ትግስት
#መሪ
No comments:
Post a Comment